ሚዛን Mizan

ሚዛን Mizan Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሚዛን Mizan, Baby & children's clothing store, Dubai.

 ===========የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰዓሊተ ምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ኃይለ መለኮትን ከአስተዳዳሪነት ያገደው ለቤተ ክርስቲያን አስቦ ወይስ ለእጅ...
25/01/2025


===========
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰዓሊተ ምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ኃይለ መለኮትን ከአስተዳዳሪነት ያገደው ለቤተ ክርስቲያን አስቦ ወይስ ለእጅ መንሻ? አባ ኃይለ መለኮት ከሥራ ለመታገዳቸው ምክንያት የሆነው ክስ የቀረበባቸው መቼ ነው?

አባ ኃይለ መለኮትን አግባብ ባለሆነ መንገድ ከዐባይ እና ከዳሸን ባንክ 47 ሚሊየን ብር ተበድረዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጉዳዩን የሚያጣራ ልዑክ የመደበ ሲሆን በወቅቱ የተመደበው ልዑክ ጉዳዩን ሲመረምር ቆይቶ ለሀገረ ስብከቱ ሪፖርት ያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

ልዑካኑ ለሀገረ ስብከት ሪፖርት ያደረጉበት ጊዜ በትንሹ ከሦስት ወራት በፊት ነው። ሀገረ ስብከቱ በወቅቱ አስተዳዳሪውን ያላገደበት ምክንያት ወቅቱ ከዝውውርና ከቅጥር የሚገኘው እጅ መንሻ የሚያባርርበት ጊዜ እንደነበር የሚታወቅ ነው። አሁን ላይ ሀገረ ስብከቱ ዝውውርና ቅጥር ማድረግ ስለማይችል ለገንዘብ ማግኛ ሲል አገልጋዮችን ከሥራ ማገዱን ሥራው አድርጎ በመንቀሳቀስ የጀመረው ልክ ዝውውሩ ከታገደበት ጊዜ አንሥቶ ነው።

ለዚህ ነው ከወራት በፊት ምንም እንዳልተፈጠረ በማድረግ ትቶ ያለፈውን የአባ ኃይለ መለኮት ጉዳይ እንደ አዲስ ተመልክቶ በዛሬው ቀን ከስራ ያገዳቸው። አንዳንዶቹ በወቅቱ ለአፍ ማዘጊያ ከ1ሚሊየን በላይ ገንዘብ ከቤተ ክርስቲያን በማውጣት ለሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች አከፋፍለዋል በማለት የካቴድራሉ አገልጋዮች ይከሳሉ።
ይህ በእንዲ እንዳለ ከፊሎችን ደግሞ ከሥራ ከምናግዳችሁና መላ ከምትሉ የትኛውን ትመርጣላችሁ በማለት በድርድር እንደሚሰሩም ተሰምቷል።

ስለዚህ የመልአከ ፀሐይ አባ ኃይለ መለኮት እግድ ለቤተክርስቲያን ታስቦ ሳይሆን አሁን ደግሞ እሳቸውን አንስቶ ቦታውን ለሌላ ሰው ለመሸጥ ታስቦ ነው ቀደም ሲል ያከፋፈሉት አንድ ሚሊየን ብር ከሦስት ወራት በላይ አገልግሎት በላይ የሚሰጥ አልሆነም።

19/12/2024

" ስለዚህ ፈሪሳውያን ደግሞ እንዴት እንዳየ እንደ ገና ጠየቁት። እርሱም። ጭቃ በዓይኖቼ አኖረ ታጠብሁም አያለሁም አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 9:15)

ቤተ ክርስቲያን አሁን የሚያስፈልጋት ካሜራ ፊት ደቅኖ በተጠኑ ለጆሮ በሚመቹ ቃላት በመግለጫ ብቻ አለሁ የሚላት ሳይሆን ተግባር ተኮር በሆነ በምእመኑ ዘንድ ቅቡልነት ያለው ያለው ሐዋርያዊት እ...
09/12/2024

ቤተ ክርስቲያን አሁን የሚያስፈልጋት ካሜራ ፊት ደቅኖ በተጠኑ ለጆሮ በሚመቹ ቃላት በመግለጫ ብቻ አለሁ የሚላት ሳይሆን ተግባር ተኮር በሆነ በምእመኑ ዘንድ ቅቡልነት ያለው ያለው ሐዋርያዊት እንቅስቃሴ የሚያደርግ ቆራጥ ሐቀኛና በዘር ጎጥ ዕይታው ያልተንሸዋረረ መሪ ነው::

Address

Dubai

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሚዛን Mizan posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share