Adama Garment Industry - AGI

Adama Garment Industry - AGI Informations de contact, plan et itinéraire, formulaire de contact, heures d'ouverture, services, évaluations, photos, vidéos et annonces de Adama Garment Industry - AGI, Prêt-à-porter et accessoires, Adama.

15/07/2026
ሜጀር ጄነራል ደረጀ መገርሳ በአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ የአረንጓዴ አሻራ አኖሩበኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ሀምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ምየመከላከያ ሰራዊት...
08/07/2026

ሜጀር ጄነራል ደረጀ መገርሳ በአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ የአረንጓዴ አሻራ አኖሩ

በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ
ሀምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም

የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሜጀር ጄነራል ደረጀ መገርሳ በአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ በመገኘት የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሂደዋል። በጉብኝታቸው ወቅትም በኢንዱስትሪው የተከናወኑ የልማትና የምርት ስራዎችን አፈፃፀም ገምግመዋል።
የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ደሱ አብዲሳ፣ ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን አጠቃላይ የምርትና የልማት እንቅስቃሴዎች በተመለከተ ለጄነራል መኮንኑ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በገለጻቸውም መሰረት፥ ተቋሙ ቀደም ሲል ከውጭ ሀገር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እየተከፈለባቸው ይገቡ የነበሩ ወታደራዊ አልባሳትን በሀገር ውስጥ ምርት ሙሉ በሙሉ መተካት መቻሉን ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ በኢንዱስትሪው ይዞታ ላይ የተጀመሩ የፍራፍሬ (ሙዝ፣ ፓፓያ፣ አቮካዶ) ልማት ስራዎች በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል።
እነዚህ የሚመረቱ የግብርና ውጤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሰራዊቱ አባላትና ለሲቪል ሰራተኞች እየቀረቡ መሆኑም በሪፖርቱ ተመላክቷል።
ሜጀር ጄነራል ደረጀ መገርሳ በበኩላቸው፤ ተቋሙ የሰራዊቱን ፍላጎት ከመሙላት ባለፈ የጦር ጉዳተኞችን በክህሎትና በሙያ በማሰልጠን እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል። ፋውንዴሽኑ "አገልግሎታችን ለጀግኖቻችን" በሚል መርህ የሰራዊቱን አባላት ለመደገፍና ለማበረታታት የሚያደርገውን እገዛ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጄነራል መኮንኑ በዚሁ ወቅት አረጋግጠዋል፡፡

ዘጋቢ ኢሳያስ መገርሳ
ፎቶ ግራፍ ማትዎስ ጌታቸው
መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ
ድረ-ገፅ
https://adamagarment.com

መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ
ፌስቡክ
https://web.facebook.com/profile.php?id=61577716505617
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/adamagarment/39

አላጌ የጦር ጉዳተኞች ማገገሚያ ማዕከል በልብስ ስፌት ለ2ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን አባላት አስመረቀ።  አደማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም አላጌ የጀግኖች አምባ የጦር ጉዳተኞ...
06/07/2026

አላጌ የጦር ጉዳተኞች ማገገሚያ ማዕከል በልብስ ስፌት ለ2ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን አባላት አስመረቀ።

አደማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

አላጌ የጀግኖች አምባ የጦር ጉዳተኞች ማገገሚያ ማዕከል ጀግና የጦር ጉዳተኞች ብሩህ ተስፋ እንዲኖራቸው በማሰብ በመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ እና በመከላከያ ፋውንዴሽን የጋራ ትብብር በአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ሲሰጥ የቆየው በልብስ ስፌት ስልጠና ተጠናቋል። በልብስ ስፌት፣ በፋሽን ዲዛይን፣ እንዲሁም በልብስ ስፌት ማሽን መካኒክ እና ኤሌክትሪካል ሙያ ያሠለጠናቸውን አባላት ነው ለምረቃ ያበቃው።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄነራል ጥጋቡ ይልማ እንደገለፁት፦ ተቋማችን መከላከያ ለሀገራችን ውድ ህይወታቸውንና አካላቸውን የገበሩ ጀግና የሰራዊት አባላትን ለመደገፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

የመከላከያ ፋውንዴሽን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የሰራዊቱን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ከመትጋቱም ባሻገር በጦር የተጎዱ የሰራዊት አባላት በስነ_ አዕምሮ በመገንባት ለነገ ህይወታቸው ብሩህ ተስፋን እየዘራ እንደሚገኝ ጠቁመው አባላቱ ከስልጠናው ባገኙት እውቀት መሰረት ራሳቸውን ማስተዳደር እንደሚችሉ ገልፀዋል።

የሰው ልጅ በህይወት ሳለ ብዙ ውጣ ውረዶች ይገጥሙታል እነዚህ ጀግኖች ግን መተኪያ የሌላትን ህይወት የሚጠይቁ በርካታ ግዳጆችን በጀግንነት በመፈፀም መስዋዕት ሆነው ሃገርን ያዳኑ ለሀገር ልዕልና ደምና አጥንት የገበሩ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው ያሉት ደግሞ የመከላከያ ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሜጄር ጄነራል ደረጀ መገርሳ ናቸው።

ጄነራል መኮንኑ ፋውንዴሽኑ "አገልግሎታችን ለጀግኖቻችን" የሚል መርህ አንግቦ ከጤና ዋና መመሪያና ከማዕከሉ ጋር በጋራ በመሆን ጀግና የሰራዊት አባላትን ለመደገፍና ለማበረታታት ሁሌም ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የአደማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ የስልጠናውን ካሪኩለም ቀርዖ በማዕከላችን ውስጥ ለሚገኙ የጦር ጉዳተኞች የክህሎት እና የሙያ ስልጠና በመስጠት ላበረከተው አሰተዋፅኦ አመስግነው ለአላጌ ጀግኖች አምባ ስታፍ አባላት እንዲሁም የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ በየጊዜው በማዕከላችን ለሚገኙ ታካሚዎች ስለጠናዎችን በማመቻቸት ላሳዩት አብሮነት ምስጋና አቅርበዋል።

ሌተናል ጄነራል ከፋለ አመዴ የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙአዳማ (ሰኔ 22/2018 ዓ.ም) — የሜካናይዝድ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ከፋለ አመዴ በመከላከያ ሠራዊ...
29/06/2026

ሌተናል ጄነራል ከፋለ አመዴ የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ
አዳማ (ሰኔ 22/2018 ዓ.ም) — የሜካናይዝድ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ከፋለ አመዴ በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ስር የሚገኘውን የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሜጀር ጄነራል ደረጃ መገርሳ እና የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ደሱ አብዲሳ ስለ ተቋሙ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ዝርዝር ገለፃ አድርገውላቸዋል።
በገለፃው ላይ እንደተጠቀሰው፤ ኢንዱስትሪው የምርት ጥራቱን ለማሳደግ እና የሲቪል እንዲሁም የወታደራዊ አልባሳት ፍላጎትን በብቃት ለማሟላት ዘመናዊ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችንና የጥራት ቁጥጥር ሥርዓቶችን ሥራ ላይ አውሏል። ተቋሙ የተደራጀ የዲጂታል መረጃ አያያዝ፣ የኔትዎርክ መሠረተ-ልማት እና የወታደራዊ አልባሳት ዲዛይንና ጥራት መፈተኛ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን በመጠቀም የምርት ሂደቱን እያዘመነ እንደሚገኝ ተብራርቷል።
ሌተናል ጄነራል ከፋለ አመዴ የፋብሪካውን የስፌት፣ የጥልፍ እና የጥራት ቁጥጥር ክፍሎችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን፤ ተቋሙ የሠራዊቱን ፍላጎት በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እያደረገ ያለውን የቴክኖሎጂ ሽግግር አድንቀዋል።

18/06/2026
በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ሰኔ  5ቀን 2018 ዓ.ምበመከላከያ  ትምህርት  እና  ስልጠና  ዋና  መመሪያ  ሎጀስቲክስ  ኮሌጅ  የአጭር  ኮርስ  ሰልጣ...
12/06/2026

በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ
ሰኔ 5ቀን 2018 ዓ.ም
በመከላከያ ትምህርት እና ስልጠና ዋና መመሪያ ሎጀስቲክስ ኮሌጅ የአጭር ኮርስ ሰልጣኞች እና የመከላከያ ስታፍ ኮሌጅ የዲግሪ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት ኢንደስትሪ ጎበኙ።
በጉብኝቱ ወቅት የአዳማ ጋርመንት ኢንደስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ደሱ አብዲሳ ለሰልጣኞቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ዋና ስራ አስኪያጁ ስለ አጠቃላይ የኢንደስትሪው የስራ እንቅስቃሴ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ ተቋሙ እየተጠቀመባቸው ያሉት ዘመናዊ የልብስ ስፌት ቴክኖሎጂዎች ለሠራዊቱ ጥራቱን የጠበቀ አልባሳት በተገቢው ፍጥነት ለማድረስና የሠራዊቱን የንብረት አቅርቦት ፍላጎት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመሙላት የሚጫወቱትን ከፍተኛ ጥቅም በዝርዝር አስረድተዋል። ከጎብኚዎቹ ለተነሱ ጥያቄዎችም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የኢንደስትሪው ምክትል ስራ አስኪያጅ ኦፕሬሽናል መቶ አለቃ ሁንዱማ ዱሬሳ በበኩላቸው፥ ተቋሙ በልብስ ስፌትና ጋርመንት ዘርፍ በአሁኑ ወቅት የደረሰበትን ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ ለጎብኚዎቹ አስረድተዋል። አክለውም ቀደም ሲል ከውጭ ሀገር ከፍተኛ ወጪ እየተደረገባቸው ይገቡ የነበሩ ወታደራዊና የተለያዩ አልባሳትን በአሁኑ ወቅት በሀገር ውስጥ የልብስ ስፌት ምርት መተካት መቻሉን በኩራት ገልጸዋል።
ልብስ ስፌት ፋብሪካ ቁጥር አንድ ኃላፊ መቶ አለቃ ጎሳ ንጉሴ እንደገለጹት፥ ተቋሙ ዘመናዊና የዘመኑን የልብስ ስፌት ማሽኖችና ቴክኖሎጂዎች ስራ ላይ በማዋል የምርት ጥራትንና የዕለታዊ ስፌት ፍጥነትን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ችሏል። ያለ ምንም ማቋረጥ (እረፍት) በከፍተኛ ቁርጠኝነት በመስራት ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን እንዲሁም ይህንን የቴክኖሎጂ አቅም በመጠቀም ተቋማዊ የጋርመንት አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገ መሆኑን አብራርተዋል።
ከጎብኚዎቹ መካከል የአጭር ኮርስ ሰልጣኝ የሆኑት ሻለቃ መሀመድ ኡመር እና የመከላከያ ስታፍ ኮሌጅ የዲግሪ አንደኛ ዓመት ተማሪ የሆኑት ሻምበል መከዳ ብርሃኑ በአዳማ ጋርመንት ኢንደስትሪ ባደረጉት ጉብኝትና በተመለከቱት የልብስ ስፌት የስራ ሂደት እጅግ መደሰታቸውን ገልጸው፤ ከተቋሙ ትልቅና ጠቃሚ የስራ ልምድ ማግኘታቸውን በደስታ ተናግረዋል።
ዘጋቢ ኢሳያስ መገርሳ

NEWS RELEASEBrigadier General Dereje Megersa Eseta, CEO of Ethiopian Army Foundation Promoted to Major General Amid Nati...
21/09/2025

NEWS RELEASE

Brigadier General Dereje Megersa Eseta, CEO of Ethiopian Army Foundation Promoted to Major General Amid Nationwide Military Elevations.

Adama, Ethiopia — September 21, 2025 — Adama Garment Industry proudly announces the promotion of its Chief Executive Officer, Brigadier General Dereje Megersa Eseta, to the esteemed rank of Major General, following a sweeping elevation of 66 senior military officers sanctioned by Prime Minister Abiy Ahmed.

On behalf of the entire workforce of Adama Garment Industry, Colonel Mekonnen Beyene Degefa, General Manager of AGI, issued a heartfelt congratulatory message:

“We extend our warmest congratulations to Major General Dereje Megersa Eseta on this well-deserved promotion. His visionary leadership and unwavering commitment to national service have inspired not only the military but also industrial unites like us. At Adama Garment Industry, we are proud to work for the Ethiopian Army Foundation in supporting our country’s defense needs. This promotion is a testament to excellence, patriotism, and dedication — values we deeply share.”

Major General Dereje Megersa Eseta has been instrumental in leading the Ethiopian Army Foundation, a strategic institution tasked with supporting the welfare, logistics, and modernization efforts of the national army. His promotion reflects not only his distinguished service record but also his leadership in advancing the Foundation’s mission during a time of evolving national security challenges.

The promotion of senior officers, including Major General Dereje, is seen as a strategic move to reinforce the leadership structure of the ENDF and ensure operational effectiveness across all regions.

Once again AGI and employees extends our heartfelt congratulations to Major General Dereje Megersa Eseta and all newly promoted officers. Their elevation marks a renewed commitment to safeguarding Ethiopia’s sovereignty and advancing its defense modernization agenda.

Media Contact:
Public Relations Office
Adama Garment Industry
Email: [email protected]

Adresse

Adama
OROMIA

Notifications

Soyez le premier à savoir et laissez-nous vous envoyer un courriel lorsque Adama Garment Industry - AGI publie des nouvelles et des promotions. Votre adresse e-mail ne sera pas utilisée à d'autres fins, et vous pouvez vous désabonner à tout moment.

Partager