ወግ ቲዩብ-weg tube

ወግ ቲዩብ-weg tube Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ወግ ቲዩብ-weg tube, Women's clothes shop, Addis Ababa.

21/03/2024
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች  በሙሉየሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያና ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ:-➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖2014/15 የኢትዮ ዩኒቨርሲቲ መግቢያናየሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ...
24/09/2022

ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ

የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያና ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ:-
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
2014/15 የኢትዮ ዩኒቨርሲቲ መግቢያና
የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ካምፖስ ጉዞ ሲያደርጉ #መያዝ #የተፈቀደላቸው፣ #መያዝ #የተከለከሉ እና #የጊዜ #ሠሌዳ እንደሚከተለው ያለው ሲሆን ተማሪዎች ከወዲሁ ራሣችሁን እንድታዘጋጁ ይሁን።

❶ #መያዝ #የተፈቀደላቸው
✡️አንሶላ፣
✡️ትራስ ጨርቅ፣
✡️የማታ ልብስ፣
✡️ደረቅ ምግብ፣
✡️ልብስ፣ቦርሳ፣
✡️የመፈተኛ ካርድ፣እርሳስ፣ላጲስ፣የማስታወሻ ደብተር፣ባዶ ወረቀት፤መጽሐፍ

❷፣ #መያዝ #የተከለከሉ
☸️ማንኛውም ድምፅ የሚቀዳ፤ቪዲዮ የሚቀዳ ወይም ፎቶግራፍ የሚያነሳ፤
☸️ካሜራ
☸️ማንኛውም ከቴሌ መስመርም ይሁን ከቴሌ ውጭ መልዕክት በድጂታል ቴክኖሎጂ መቀበያ ወይም ማስተላለፊያ ውጤቶች(ታብሌት፣ኮሚፕዩተር፣ላብቶፕ፣ ስልክ፣አይፓድ፥ሃርድ ዲስክ፣ፍላሽ)

❸ #የጊዜ #ሠሌዳ
✡️ማህበራዊ ሳይንስ $social science dep't
➤26_28/1/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ
➤29/01/2015 ኦሬንተሽን
➤30/01/2015_02/02/2015 ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል።

✡️የተፈጥሮ ሳይንስ Natural Science dep't
➤05_06/2/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ
➤07/02/2015 ኦሬንተሽን
➤08/02/2015_11/02/2015 ፈተናው
የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል።

ተማሪዎች መረጃው እንዲደርሳቸው ሼር ያድርጉ።
መረጃው ከትምህርት ሚኒስተር ነው የተገኘው።

ፈተናውን በመረጋጋት አና በትኩረት በመስራት ጥሩ ውጤት እንድታመጡ እንመኛለን!

መልካም እድል!

24/09/2022

መንታ መንገድ - ክፍል 2
ክፍል ሁለት
በወግ ቲዩብ
ቤተሰብ የሁሉም ነገር መሰረት ነዉ። መልካም ባልሆነ ቤተሰብ ዉስጥ ያደገ ልጅ መጥፎ ቢሆን አይገርምም።
ጊዜዉ እየገፋ ሲመጣ የምሳተፍባቸዉ ሀይማኖታዊም ሆኑ የኪነ ጥበብ ቡድኖች ለጊዜዉ ያለሁበትን ጭንቀት ከማስረሳት በዘለለ ግላዊ ፍላጎቴን ማርካት እንዳልቻሉ ተገነዘብኩ። እያንዳንዱን ጉዳዬን የማማክረዉ ሰዉ ሊኖር ይገባል። በሰዓቱ የነበርኩበት የእድሜ ደረጃ እንደተራ ሰዉ ፍቅረኛ መያዝ የሚል አማራጭን ቢያቀርብልኝም ከሴት ጋር ያን ያህል ቀረቤታ ስላልነበረኝ ከወንድ ጓደኞቼ ጋር ያለኝን ትስስር ለማጠናከር ወሰንኩ። በሰርግ ምክንያት ከተዋወቅኩት አንድ ጓደኛዬ ጋር የወንድም ያህል ተቀራረብን ሚስጥሬን ሁሉ የማካፍለዉ ለሱ ሆነ። ጭንቄንም ቢሆን ከፈጣሪዬ ጋር በግንባሬ ተደፍቼ ከመከርኩበት በኋላ ከሱ ጋር እወያይበታለሁ። ጓደኛዬ ሰዒድ ይባላል። እሱን ከተዋወቅኩ በኋላ ትንሽ ጭንቀቱም ቀለል አለልኝ። ከጎንህ የሚያማክርህ አንድ ታማኝ ወንድም እንደማግኘት የሚያስደስት ነገር የለም።
እድሜዬ አስራዘጠኝ ሲሆን ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ካምፓስ ተመድቤ ቱሪዝም እና ሆቴል ማኔጅመንት ማጥናት ጀመርኩ። ባህር ዳር በጣም ዉብ ከተማ ነች። መንገዶቿ በአረንጓዴ ልማት ያጌጡ እና ፅዱ ናቸዉ። ኑሮ ከሸገር ጋር ሲነፃፀር በጣም ርካሽ ነዉ። አየሯ ከአዲስ አበባ ጋር ሲወዳደር ትንሽ ሙቀታማ ከተማ ናት። የጣና ሀይቅ አይን አይቶ የማይጠግበዉ ... ብቻ ምንልበላችሁ በጣም ብዙ ዉበቶች በአንድነት የሰፈሩባት ለምለም ምድር ናት።
የተመደብኩበት ፔዳ ካምፓስ ደግሞ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ካሉት ካምፓሶች ትልቁ ካምፓስ ነዉ። የተፈጥሮ ሳይንስናየማህበራዊ ሳይንስ ትምህርቶች ይሰጡበታል። ግቢዉ ዉስጥ ብዙ ካምፓሶች አሉ። ግቢዉም እንደ ከተማዋ አረንጓዴ ነዉ። የፔዳ ካምፓስ እንደኔ ሰላም ከሌለዉ ቤተሰብ ለመጣ ሰዉ ትልቅ ሰላም ያለዉ ቦታ ነዉ። ትምህርት ተጀምሮ ጥቂት እንደተማርን ከክፍል ተማሪዎች ጋር መግባባት ጀመርን። ትንሽ ቆንጆ ነገር ነኝ በዚህ ምክንያት ወንዶቹ "አክረም ቺኳ" እያሉ ይጠሩኛል። ሲጀመርም የትምህርት ዘርፋችን አምሮ መታየት እንደ መስፈርት የሚታይበት ነበርና የሴቶቹ አለባበስ እና አኳኋን ቀልብ የሚያስት ነበር። ከአለባበስ ጀምሮ እስከ ፀጉር ስታይል ሁሉም ራሳቸዉን መኳል ስራቸዉ ነዉ። ወንድ ሆኖ እኛ ክፍል ዉስጥ መማር የማይፈልግ ያለ አይመስለኝም። ወንዶች ትንሽ ስለሆንን በሴቶቹ ተከበን ነዉ የምንማረዉ። ብዙዎች የኛን የትምህርት ዘርፍ የሴቶች ነዉ ይሉታል። ከአዲስ አበባ ከ500 በላይ ኪሎ ሜትሮችን ርቄያለሁ በዚህ ሰዓት ቤተሰብ አጠገቤ የለም። ፈጣሪዬን ካልፈራሁና ለራሴ ክብር ከሌለኝ የፈለግኩትን ማድረግ እችላለሁ። ጓደኛዬ ሰዒድ ከአዲስ አበባ ሆኖ አሁንም በስልክ ያማክረኛል።
ሀያት ፣ ሀጅራ እና ራሄል የቅርብ ጓደኞቼ ሆኑ። በዩኒቨርሲቲ ካገኘኋቸዉ ልጆች በሳል ብዬ የቀረብኳቸዉ እነሱን ነዉ። ከእህቶቼ ጋር መልካም ቅርርብ ስላልነበረኝ የእህትነት ፍቅርን ከነሱ ለማግኘት ብዬ በደንብ ቀረብኳቸዉ። ሀጅራ ረጋ ያለችና ምክር የምታበዛ ጠይም የኮምቦልቻ ልጅ ናት። ሀያት ሲፈጥራትም ሳቂ ብሎ የፈጠራት ይመስል ከፊቷ ላይ ፈገግታ ከንግግሯ መሀል ሳቅ የማይጠፋ የሸገር ቆንጆ ናት።
https://t.me/wegtube
https://t.me/wegtube
https://t.me/wegtube
https://t.me/wegtube
ቀጣይ ክፍል ለማግኘት ቴሌግራም ይቀላቀሉን

የ4የካፓስ ተማሪወች መንታ መንገድየተሰኘ የሂወት ታሪክአለ ካነበባችሁ ልልቀቅላችሁ???እኔን ራሱ በፍቅር  ያበረከከ ምርጥ ታሪክ ነው😭////መንታ መንገድ//ክፍል አንድ(ወግ ቲዩብ)ከልጅነቴ ጀ...
24/09/2022

የ4የካፓስ ተማሪወች መንታ መንገድ
የተሰኘ የሂወት ታሪክ
አለ ካነበባችሁ ልልቀቅላችሁ???
እኔን ራሱ በፍቅር ያበረከከ ምርጥ ታሪክ ነው😭
////መንታ መንገድ//
ክፍል አንድ
(ወግ ቲዩብ)
ከልጅነቴ ጀምሮ ቤት ዉስጥ ጭቅጭቅ እያየሁ ነዉ ያደግኩት። ትንሽዬ የጦርነት ሜዳ ውስጥ! እናቴ ምላሷ አይጣል ነዉ። አባቴ ደግሞ የእናቴ ምላስ ይመስገንና ሳይደበድባት ነግቶ አይመሽም። በርግጥ አባቴ ከእናቴ ጋር ለመጋጨት የእሷ ነገረ ስራ አስገድዶት እንጂ ሳትደርስበት ደርሶባት አያዉቅም። እኔም ድብድቡን ወንበር ስር መሽጌ እየተመለከትኩ አደግኩ። ፀባቸዉ ገና ሲጀመር እንባዬ ከአይኖቼ ዱብ ዱብ እያለ ወንበር ስር ተደብቄ አያለሁ። ሁሌም ሰላም የለኝም። አንዳንዴ የእናቴ ተግባር እኔን ራሱ በጣም ያበሳጨኝ ነበር። እንግዳ በሚመጣበት ጊዜ አሊያም ከጓደኞቿ ጋር ስትሆን የአባቴን የግል ሚስጥር ሳይቀር ትለፈልፋለች። እድሜዬ እየጨመረ ሲመጣ እና ነገሮችን ላቅ ባለ እይታ ማገናዘብ ስጀምር የእናቴ ተግባር ምን ያህል መጥፎ እንደሆነ ስለተረዳሁት የአባቴ ድብደባ ሲያንሳት ነዉ ወደሚል ድምዳሜ ደረስኩ። ምንም እናት ብትሆንም በፍፁም ለልጆቿ አርዐያ መሆን እንደማትችል ከስነ ምግባር ዝቅጠቷ ተረዳሁ። ቤት ዉስጥ ያለነዉ ሶስት ልጆች ነን። ሁለቱ እህቶቼ ናቸዉ። ታዲያ እናቴ ለእህቶቼ ስለ አባቴ መጥፎ አስተሳሰብ እንዲኖራቸዉ የሆነ ያልሆነዉን እየነገረች ቤት ዉስጥ ትርምስ መፍጠር ጀመረች። እህቶቼ የእናቴ ኮፒ ሆኑ። በዚህም ምክንያት ከቤታችን ዉስጥ ሰላም ጓዙን ጠቅልሎ ወጣ። አባቴ በእህቶቼ ሳይቀር በጣም መናቅ ጀመረ። እኔ እናቴ እያደረገች ያለችዉ ነገር ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ ላስረዳት ብሞክርም "አንተ የአባትህ ኮፒ ነህ!" እያለች ምክሬን አልቀበልም አለች። እናቴ ለአባቴ ልክ እንደ ልብስ ሆና ሚስጥሩን መሸሸግ እና ክፍተቱን መሙላት ሲገባት የሱን ስም ለማጥፋት መቅጠፍ ድረስ ሄደች። ስግደት ለሰዉ ተገቢ ስላልሆነ እንጂ እንድትሰግድለት ልትታዘዝለት የነበረችዉ ሚስት ባሏን በጣም መናቅና ዉሳኔዎቹን አለማክበር ጀመረች። የትዳር መሰረት ተናጋ! ህፃናት ልጆች በእናትና በአባት መካከል ጣልቃ ሲገቡ የትዳር መሰረት መናጋቱ የማይቀር ነዉ። እኔ ግን የሚገርመኝ የአባቴ ትዕግስት ነዉ። ለምን አይፈታትም? እኔ ብሆን የሱን ያህል የምታገስ አይመስለኝም።
እድሜዬ ከፍ ብሎ የአስራሁለተኛ ክፍል ተማሪ ስሆን ቤት መግባት የሚባል ነገር አስጠላኝ። ጠዋት ከቤት የወጣሁ ማታ አራት ሰዓት ወደ ቤት ብመለስ ነዉ። ማታ ወደ ቤት ስመለስ ልክ ወደ መገደያዉ ስፍራ እንደሚወሰድ እስረኛ እየቀፈፈኝ ነዉ። ወደ ቤት ላለመመለስ ስል ቀኑን በተቻለኝ መጠን ራሴን በተለያዩ ነገሮች ቢዚ በማድረግ አሳልፋለሁ። ከቤተሰቤ ያጣሁትን ፍቅር ፍለጋ የተለያዩ ሀይማኖታዊ ክበቦች ላይ እንዲሁም የኪነ ጥበብ ማህበሮች ላይ መሳተፍ ጀመርኩ። ብዙዎቹ ጓደኞቼ ቤታቸዉ ዉስጥ ያላቸዉ ሰላም እና የቤተሰብ ፍቅር ምን ያህል ትልቅ ፀጋ እንደሆነ አይረዱትም። እኔን በተለያዩ ክበቦች ላይ በንቃት ተሳታፊ እንደሆንኩ ሲመለከቱ በጥንካሬዬ ይገረማሉ። እኔ ከቤቴ ያጣሁትን ፍቅር እና ሰላም ፍለጋ እነዚህ ክበቦች ዉስጥ መመሸጌን አያዉቁም።
ይቀጥላል...
https://t.me/wegtube
https://t.me/wegtube
https://t.me/wegtube
https://t.me/wegtube
ቀጣይ ክፍል ለማግኘት ቴሌግራም ይቀላቀሉን

አዲስ ተከታታይ ትረካ
23/09/2022

አዲስ ተከታታይ ትረካ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወግ ቲዩብ-weg tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share