08/07/2023
በርግጥ እምነት አንድ ነገር ነው ። የማይከፈል ። የማይታበል ። የማይሸጥ የማይለወጥ ። የማይፋቅ ። የማይጣመም ። የማይቃና ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አባት እና ልጅ በኩርሲ ወንበር ላይ ተቀምጠው ቡና ይጠጣሉ ።
ልጅ ፡ " አባየ "
አባት ፡" አቤት ዉዷ ልጀ "
ልጅ ፡ " አንድ ሲደመር አንድ ስንት ነው ?"
አባት ፡" አንድ ነው ።"
ልጅ ፡" ኧረ አባ ሁለት ነው ። "
አባት :" እሱ የቁጥር ህግ ነው "
ልጅ ትንሽ እንደማኩረፍ ብላ " እሽ አንድ ሲደመር ሁለትስ? "
አባት ፡" አሁንም አንድ ነው ።"
ልጅ ፡ " ኧረ አባ ውሃ ነው ። ከአንድ ኦክስጅን ከሁለት ሃይድሮጅን ስለሚሰራ ! "
አባት ፡" እሱም የኬሚስትሪ ህግ ነው ፡፡ "
ልጅ ግራ ተጋብታ ፡ " እሽ ያንተ ህግ የማነው ?"
አባት ፡" የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ።"
ልጅ ፡" እኮ ከወዴት ነው ?"
አባት ፡" ከፈጣሪ ነው ልጀ ።" ብሎ ይመልሳል ።
የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ፈጣሪን መፍራት ነው ። ሌሎች ሰዎች ለራሳቸው እንዲመች የቆጠሯቸው መሰናክሎች ናቸው ። የፈጣሪውን ህግ የሚያከብር አይሰርቅም ። አይታበይም ። አይገልም ። የሰው ሚስት አይደፍርም ።።።። ገፅ 123
አንድ ወቅት በወርሃ ፆም አንድ መለኩሴ ሲጓዙ አንድ ጠብደል መሃይም ዛፍ ተደግፎ ወተት ሲጠጣ ይደርሱበታል ። ቄሱ ይቀርቡት እና
" አንተ ምን ትጠጣለህ ?" ብለው ይጠይቁታል ።
ጥርሱን ፈገግ አድርጎ " ወተት ነው ። ይጠጣሉ አባቴ ?" ይላቸዋል ። የሚጠጣበትን እያሳያቸው ።
" በስመ አብ ፡ በወርሃ ፆም ምነው ምነው ፃ መንፈሰ ርኩስ " ብለው ከቅላቸው ፀበል ረጭተውት ፡ ከፀበሉ አጠጥተውት ይሄዳሉ ።
ከፊቱ ዘወር ሲሉ " አልቻልሁም አባቴ " ብሎ ብልቃጥ ወረወረባቸው ።
ቄሱ ደርሰው ሲያዩት መርዝ ጠጥቶ ነበር የወደቀ ። በዚህ ጊዜ ፈጥነው ካስጣሉት ወተት ግተውት ይጠብቁት ጀመር ።
ትንሽ ቆይቶ ልጅ ይነቃል ።
" ለምን በፆሙ ወተት አጠጡኝ ?" ሲል ጠየቃቸው ።
ቄሱም " አንደኛ ፀበሉን በመርዙ ስላረከስኸው ።ሁለተኛ ደግሞ ሳትፈልግ አማኝ ከምቶን ፈልገህ አህዛብ ብቶን ይሻላል ። በል በምታምነው ኑር ። " ብለውት ይሄዳሉ ።
ገፅ 39
ሁሉም ሰው የራሱ መንገድ አለው ። ነገር ግን ሌሎችን በመንገዱ ላይ እየረገጠ መራመድ ከጀመረ በራሱ መንገድ ሳይሆን በሌሎች ላይ እየተረማመደ ነው ።
ከአዳም ኦጅ አሻራ ለቅምሻ የተቀነጨበ ።
ዘገየ ታዴ ( engineer )