My - Journey vintage " የጉዞ ማስታወሻዎች "

My - Journey vintage " የጉዞ ማስታወሻዎች " Our premier objective here is that, w're aimed to share our trip vintage photos, video and any othe

African Union Headquarters_Addis Ababa     View
09/05/2024

African Union Headquarters_Addis Ababa View

31/12/2022
My home village
31/12/2022

My home village

በሄሊኮፕተር ብቻ የሚጎበኘው ፓርክ ይህ የኢትዮጵያ ፓርክ በዱር እንስሳት ስብጥር ከአፍሪካ ሁለተኛ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ከአዲስ አበባ በ 776 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምዕራብ ኢትዮጵያ ...
07/02/2021

በሄሊኮፕተር ብቻ የሚጎበኘው ፓርክ

ይህ የኢትዮጵያ ፓርክ በዱር እንስሳት ስብጥር ከአፍሪካ ሁለተኛ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ከአዲስ አበባ በ 776 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ የዱር እንስሳትን ለመጠበቅ በሚል በ 1960 ዓ.ም መቋቋሙን ሰነዶች ይገልጻሉ፡፡

ይህ ፓርክ 4 ሺ 575 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ፣ 69 አይነት አጥቢዎች ፣ 327 የተለያዩ የወፍ ዝርያዎች እና 7 አይነት ተሳቢ እንስሳት እንዲሁም 493 የእፅዋት ዝርያዎች በውስጡ ይገኛሉ፡፡ ዋልያ አይቤክስ ፣ የዱር አጋዘን ፣ የዱር አንጋላ ፣ ጎሽ ፣ ቀይ ቀበሮ እና ሌሎችም በፓርኩ ከሚገኙ እንስሳት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ይህ ፓርክ በዱር እንስሳት ስብጥር ከአፍሪካ ሁለተኛ እንደሆነም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ፓርኩ ምንም እንኳን በውስጡ ብዙ አይነት የዱር እንስሳት ቢኖሩትም እየተደረገ ያለው ከመጠን ያለፈ ሕገ-ወጥ አደን የፓርኩን ህልውና እየተፈታተነ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማት እና ጥበቃ ባለስልጣን ባለፈው ዓመት ብቻ በፓርኩ ወስጥ የሚገኙ አምስት ዝሆኖች መገደላቸውን አስታውቋል፡፡ ባለሥልጣኑ "በጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ የብዝሃ ህይወት ሀብት ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ትብብር ያስፈልጋል" ብሏል።

የፓርኩ ጽህፈት ቤት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ሄኖከ ታምሩ ፣ በፓርኩ በሚገኙ የእንስሳት ሀብት ላይ ከፍተኛ ህገ ወጥ አደን እየተካሄደ መሆኑን ገልጸው በተለይም የነጭ ጆሮ ቆርኪ እና ዝሆኖች ላይ ከፍተኛ አደን እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አቶ ሄኖክ "ችግሩን ለመከላከል ጥረት እየተደገ ቢሆንም የተፈለገውን ያህል ለውጥ ማምጣት አልተቻለም" ብለዋል።

በፓርኩ ዙሪያ በቅርቡ በተደረገ ውይይት ላይ ፣ የቀድሞ የፓርኩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የአሁኑ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋልዋክ ኮርት (ዶ/ር) ፣ ቀደም ሲል በፓርኩ ከ550 በላይ ዝሆኖችና ከ 1 ሚሊዮን በላይ የነጭ ጆሮ ቆርኪዎች እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡ አሁን ግን የዝሆኖችም ሆነ የነጭ ጆሮ ቆርኪና የሌሎች እንስሳት ቁጥር እየቀነሰ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሎው ኡቡፕ (ዶ/ር) ደግሞ ፣ የፓርኩን ወሰን ግምት ውስጥ ያላስገባ የግብርና ኢንቨስትመንት፣ ህገ ወጥ ሰፈራ ፣ አደንና ሌሎች ድንበር ዘለል የአርብቶ አደሮች ጥቃት መኖሩን በውይይቱ ወቅት የገለጹ ሲሆን ይህን ለመከላከል እንደሚሰራ ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳንን የሚያዋስነው ባሮ አኮቦ ወንዝን በማቋረጥ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚገመት ነጭ ጆሮ ቆርኬዎች በክረምት ወቅት ከጋምቤላ ብሄራዊ ፓርክ ወደ ደቡብ ሱዳን ቦማ ብሔራዊ ፓርክ የሚያደርጉት የስደት ጉዞ አስደማሚ ትዕይንት ሲሆን ይህም ከዓለም ሁለተኛው መሆኑን የፓርኩ ጽህፈት ቤት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ሄኖከ ታምሩ ለአል ዐይን ተናግረዋል፡፡ በዚህ ወቅትም የእንስሳቱ የስደት ትዕይንት በሄሊኮፍተር የሚጎበኝ ፣ ደማቅና ማራኪ እንደሆነም ይገለጻል፡፡

ታንዛኒያና እና ኬንያን የሚያዋስነው ማራ ወንዝን በማቋረጥ ከታንዛኒያው ሰረንጌቲ ብሔራዊ ፓርክ ወደ ኬንያው ማሳማራ ብሔራዊ ፓርክ እርጥብ ሳር ፍለጋ በየአመቱ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዋይልድ ቢስቶች የሚያደርጉት የእንስሳት የስደት ትዕይንት በዓለም ላይ አንደኛ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን የኢትጵያው ደግሞ ሁለተኛ ነው፡፡

በክረምት ወቅት የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ በውሃ ስለሚጥለቀለቅ እንስሳቱ ወደ ደቡብ ሱዳን ይሻገሩና ክረምቱ ሲያልፍ ተመልሰው ወደ ቀደመ ስፍራቸው ተመልሰው እንደሚመጡ አቶ ሄኖክ ገልጸዋል፡፡ በፓርኩ የመሰረተ ልማት ችግር በመኖሩ ትዕይንቱን ለመመልከት ቱሪስቶች ወደስፍራው መምጣት አለመቻላቸውን የገለጹት አቶ ሄኖክ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች አካባቢውን ለማልማት ቢያስቡም በመሰረተ ልማት ችግሮች ምክንያት ፓርኩን ሳይመርጡት ቀርተዋል ብለዋል፡፡ በሄሊኮፕተር ብቻ የሚጎበኘው ይህ ፓርክ በቀጣይ በሌሎች የትራንስፖርት አማራጮችም መጎብኘት ይችል ዘንድ የመንግስትን እጅና ውሳኔ እየጠበቀ ነው፡፡

ምንጭ :-

ይህ የኢትዮጵያ ፓርክ በዱር እንስሳት ስብጥር ከአፍሪካ ሁለተኛ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ

እንዴት ነው ?
23/11/2020

እንዴት ነው ?

22/11/2020
ከወልቂጤ አዲስ አበባ  እየተጓዝን ነው። ጉዟችን በጨረፍታው የምትመለከቱትን ይመስላል።
21/11/2020

ከወልቂጤ አዲስ አበባ እየተጓዝን ነው። ጉዟችን በጨረፍታው የምትመለከቱትን ይመስላል።

አሁን ዘቢዳር /ጠረጋ
21/11/2020

አሁን ዘቢዳር /ጠረጋ

16/11/2020

Part - 3
ዘቢዳር ተራራ በወፍ በረር ጥቅምት 26-2013
Zebidar mountain birds eye view tikimt 26 -2013
fb.me/MubarekDelil.vintages

Part  - 2ዘቢዳር ተራራ በወፍ በረር ጥቅምት 26-2013Zebidar mountain birds eye view tikimt 26 -2013fb.me/MubarekDelil.vintages
14/11/2020

Part - 2
ዘቢዳር ተራራ በወፍ በረር ጥቅምት 26-2013
Zebidar mountain birds eye view tikimt 26 -2013
fb.me/MubarekDelil.vintages

Part  - 1ዘቢዳር ተራራ በወፍ በረር ጥቅምት 26-2013Zebidar mountain birds eye view tikimt 26 -2013
10/11/2020

Part - 1
ዘቢዳር ተራራ በወፍ በረር ጥቅምት 26-2013
Zebidar mountain birds eye view tikimt 26 -2013

Address

Addis Ababa
ADD

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when My - Journey vintage " የጉዞ ማስታወሻዎች " posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category