Abyssinia soft toys አቢሲኒያ አሻንጉሊቶች

Abyssinia soft toys አቢሲኒያ አሻንጉሊቶች Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Abyssinia soft toys አቢሲኒያ አሻንጉሊቶች, Baby & children's clothing store, Addis Ababa.

28/09/2024
04/04/2024

“መሰንቆን እንደ ሰው የሚያናግሩት” - አርቲስት ለገሰ አብዲ

| መሰንቆ እሳቸው እጅ ስትገባ ሙሉ ክብሯን ታገኛለች፡፡ በጆሮ ተሻግሮ ከልብ የሚደርሱ ጥዑም ዜማዎችን ታፈልቃለች፡፡ መሰንቋቸውን እንደ ሰው ነው የሚያነጋግሩት ይባልላቸዋል፡፡ ከዜማቸው ባሻገር ጥልቅ መልዕክት ያላቸውን ግጥሞች ሲደርሱም ወደር የላቸውም፡፡ ለአብነትም «አማ ስኳሬ» እና «አወይ የገላ ሳሙና» የተሰኙትን የጥላሁን ገሠሠ ታዋቂ የዘፈን ግጥሞችን የደረሱት እሳቸው ናቸው። ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ማደግ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ - አርቲስት ለገሰ አብዲ / አባ መሰንቆ

በ1931 ዓ.ም፣ በሰላሌ አውራጃ፣ ያያ ቀጨማ ተብሎ በሚታወቀው ቦታ ነው የተወለዱት፡፡ ለወላጆቻው ብቸኛ ልጅ ነበሩ፡፡ የአባቱ የአቶ አብዲ ዳዲ ወዳጅ የነበሩት ባለመሰንቆው ወሰኑ ዲዶ፣ ለገሰ ገና በልጅነቱ በመሰንቆ ፍቅር እንዲወድቁ ምክንያት እንደሆኑት ይነገራል። ከዚያ ጊዜ ጀምሮም መሰንቆ የለገሰ መለያ ሆነ። በሠርግና በሌሎች ዝግጅቶች ላይ እየተገኙ መጫወት ጀመሩ።

ከትውልድ አካባቢያቸው ከሰላሌ ተነስተው ወደ ወሊሶ፣ ጅማ፣ ወለጋ፣ ኢሉባቦርና ሌሎች አካባቢዎች ድረስ በመሄድም መሰንቆን ይጫወቱ ነበር። በኋላም ወደ አዲስ አበባ መጡ፡፡ በኋላም ክብር ዘበኛን በመቀላቀል ካሳ ተሰማንና ጥላሁን ገሠሠን ጨምሮ ከሌሎች አንጋፋ ድምፃውያን ጋር የመሥራት እድል አገኙ፡፡

ነገር ግን የኦሮምኛን ሙዚቃን ከ60 ዓመታት በላይ በመሰንቆ የተጫወቱት አርቲስት ለገሰ ሌላው ቢቀር ጡረታቸው እንኳ ሳይጠበቅላቸው ማለፋቸውን ልጆቻቸው ይገልፃሉ፡፡

ልጃቸው ሀብታሙ ለገሰ ስለዚሁ ጉዳይ ሲያስረዳ አርቲስት ለገሰ ከሀገር ፍቅር እስከ ብሔራዊ፣ ከማዘጋጃ ቤት እስከ ሒልተን ሆቴል እየተዘዋወሩ ድንቅ ተሰጥቷቸውን ከ60 ዓመታት በላይ ሲያሳዩ የቆዩ ቢሆንም መጨረሻ ላይ ግን ጡረታቸው አልተጠበቀላቸውም፡፡

ከዚህ ባሻገር ሲገለገሉባቸው የነበሩት ሁለት መሰንቆዎችም መቀመጫ አጥተው ቤት ውስጥ ተሰቅለው እንደሚገኙ ተናግሯል፡፡ የተለያዩ አልባሳት፣ ጨሌዎች፣ ጎፈሬዎች እና በርካታ ሽልማቶችም እንዳሉ ገልጾ እንደ ታሪክ ኤግዚቢሽን ቢቀመጡ መልካም እንደሆነ አስረድቷል፡፡

የለገሰ አብዲ የልጅ ልጅ የሆነው ናትናኤል ሀብታሙም ከእሳቸው ስር ስር እያለ ማደጉን አስታውሶ አባታችን ለቤቱና ለልጆቹ የነበረው ፍቅር ይለይ ነበር ይላል፡፡ ነገር ግን በሰራው ስራ ልክ ስሙ ተነስቷል ብሎ እንደማያስብም ገልጿል፡፡

አርቲስት ለገሰ ምንም ዓይነት ዘመናዊ የሙዚቃ ትምህርትን ሳይማሩ አራቱንም የሙዚቃ ቅኝቶች በመጫወት የሚታወቁት አርቲሰት ለገሰ አብዲ፤ በመድረክ ላይ ካቀረቧቸው ዘፈኖች በተጨማሪ አንድ የሸክላ፣ አስራ አንድ የካሴት እንዲሁም አንድ ሲዲ (CD) እና ቪሲዲ (VCD) በማሳተም ሙዚቃዎቻቸውን ለአድማጭ አድርሰዋል።

ጥበብን፣ ፍቅርን፣ ውበትን፣ አካባቢን፣ ባህልን፣ ማህበራዊ ጉዳዮችን እያነሱ በመሰንቋቸው ተጫውተዋል፤ በጥበብ ማኅበረሰቡን ሲያገለግሉ ቆይተዉ ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም በተወለዱ በ80 ዓመታቸው ማለፋቸው ይታወሳል፡፡

በፈቲያ ሁሴን

03/04/2024
አቢሲኒያ አሻንጉሊቶች
17/02/2024

አቢሲኒያ አሻንጉሊቶች

24/12/2023

Address

Addis Ababa

Telephone

+251931484970

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abyssinia soft toys አቢሲኒያ አሻንጉሊቶች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Abyssinia soft toys አቢሲኒያ አሻንጉሊቶች:

Shortcuts

Share