Hanan Taha

Hanan Taha Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hanan Taha, Women's clothes shop, Addis Ababa.

03/08/2026

በሃላል መንገድ ኒካህ ማሰር አጅር የሚያስገኝና ሪዝቅን የሚያሰፋ ሲሆን

በተቃራኒው ከኒካህ በፊት የሚደረግ የሃራም ግንኙነት ግን ወንጀል ሲሆን ሪዝቅንም ያጠባል..‼️

ሞትን በብዛት የሚያስታውስ ሰው በሦስት ነገሮች ይከበራል።👉እስቲግፋር በፍጥነት ያደርጋል።👉ልቡ ይለሰልሳል (ይረጋጋል፣ ይታዘዛል)።👉በኢባዳ ንቁና ታታሪ ይሆናል።
02/08/2026

ሞትን በብዛት የሚያስታውስ ሰው በሦስት ነገሮች ይከበራል።
👉እስቲግፋር በፍጥነት ያደርጋል።
👉ልቡ ይለሰልሳል (ይረጋጋል፣ ይታዘዛል)።
👉በኢባዳ ንቁና ታታሪ ይሆናል።

   🕌 ቀኑ ማክሰኞ ቀን ነበር በሪያድ ከተማ የተከሰተው አደጋ የ Mercedes እና Lexus መኪና ፊት ለ ፊት ተጋጭተው ነበር.."አምቡላንስ አየሁ ከዛም የተሰበሰበ ህዝብ፣አንድ ወጣትን ል...
02/08/2026


🕌
ቀኑ ማክሰኞ ቀን ነበር በሪያድ ከተማ የተከሰተው አደጋ
የ Mercedes እና Lexus መኪና ፊት ለ ፊት ተጋጭተው ነበር..

"አምቡላንስ አየሁ ከዛም የተሰበሰበ ህዝብ፣

አንድ ወጣትን ልጅ እድሜው 26 አካባቢ የሆነን ከመኪናው ሲያወጡት አየው፡፡

ሰውነቱ በደም ተሸፍኗል አካላቱ ተቆርጠዋል፣ እግሩም ጭምር ተቆርጧል እና እሱም እየጮኸ ነው"፡፡ ይለናል የታሪኩ ዘጋቢ

ልጁም ወደ ወንድሙ እየተመለከተ ምናልባትም የቅርብ ቤተሰቡ ይሆናል

"መሞት አልፈልግም፣በጣም ፈርቻለሁ ፣ እሳት ነው ምገባው እኮ" ይለዋል

እዛው ተኝቶም እየጮኸ "ሙሀመድ እኔኮ አልሰግድም ነበር ምናልባትም አካል ጉዳተኛ እሆን ይሆናል መሞት ግን አልፈልግም፣ ከዚህ ቡሃላ እሰግዳለሁ፣ ወላሂ እሰግዳለሁ ብቻ ግን መሞት አልፈልግም" ይላል

ሰወችም ተሰበሰቡ፣ እኔም ሁሉንም ክስተት እየተመለከትኩ አዛው ቆምኩ፣ በጣምም ፈርቻለሁ፡፡

በቦታው ላይ የሚታየው በሙሉ እጅግ በጣም ይዘገንናል፣ ያስፈራል

የልጁም መድማት እየጨመረ መጣ ጩኸቱም _ ቀጠለ ሰውነቱም ወደ ሰማያዊ እየጠቆረ ሄደ፡፡

ሊያድኑት ግን አልቻሉም

አብሮት የነበረውም ልጅ እያለቀሰ “እሺ ሸሀዳ በል ከሊማዉን በል…በል” ይለዋል ልጁ ግን እየጮኸ ነበር ምላሱም ከሊማውን ልትል አልቻለችም

አላሁ አክበር፣ በጣም ፈርቶ ነበር፣ ግን ነፍሱም ተወሰደች ድምፁም ተሰወረ

ግን....ግን ሸሀዳውን ማለት አልቻለም ነበር

ከዚያም አልተንቀሳቀሰም፣ ሰውነቱም ደርቆ ቀረ

ዶክተሮቹም ያላቸውን መሳሪያ ሁሉ አወጡ ልጁንም ቃሬዛ ላይ አስቀመጡትና ጭንቅላቱን ሸፈኑት

ወደ ወንድሙም በመዞር “አለቀ” - “ወንድምህ የለም ዱዓ አድርግለት ልናድነው አልቻልንም ምክንያቱም ከጭንቅላቱ እና ከሰውነቱ ብዙ ደም ፈሷል” አሉት፡፡

ዘጋቢውም ይለናል፦" በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ከፊት ለፊቴ እያየሁት ግን ሸሀዳን ለማለት ሳይችል ሞተ እህት ወንድሞቼ ሞት ድንገት ነው የሚመጣው፣ ሰላታችሁን ግን ጠብቁ፣ በፍፁም ከነገ ጀምሮ እሰግዳለሁ አትበሉ፡፡

የመጨረሻ ቀናችሁ መቼ እንደሆነ ማንም አያውቅም እኔም ከዚህ ክስተት ቡሃላ መተኛት አልቻልኩም እንደ ህፃን ሳለቅስ ነበር ልጁን ባላውቀውም ቃላቶቹን ግን በደንብ አስታዉስ ነበር...” እሰግዳለሁ፣ ወላሂ ከዚህ ቡሃላ እሰግዳለሁ፣ መሞት ግን አልፈልግም..….”😭😭

ያ አላህ መጨረሻችንን አሳምርልን ከመጥፎ አሟሟትም ጠብቀን

አንብባችሁ ለሌሎችም ሼር አድርጉ ምናልባትም በዚህ ታሪክ የ1 ሰውን ህይወት ማቃናት እንችል ይሆናል እንሻአላህ፡፡

28/07/2026

ቸኩለንም አይተነዋል ዘግይተንም አይተነዋል ሁሉም የሚሆነው በአላህ ፍቃድነው ::ኢንሻ አላህ

Answer for me plzzz
28/07/2026

Answer for me plzzz

25/07/2026

ሁላችንም የወደፊት ጀናዛዎች ነን ፣ እኛ የዱንያ አይደለንም ዱንያም የኛ አይደለችም።

25/07/2026

وفي يوم التروية

- ‏رَبِّ إِنِّي لِمَا أَنزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ
- رَّبِّ أَنزِلْنِي مُنزَلا مُّبَارَكًا وَأَنتَ خَيْرُ الْمُنزِلِينَ
- ‏رَبِّ اغْفِرْ لِي وَلِوَالِدَيَّ
- رَبِّ اجْعَلْنِي مُقِيمَ الصَّلَاةِ وَمِنْ ذُرِّيَّتِي رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَاءِ
- رَّبِّ أَدْخِلْنِي مُدْخَلَ صِدْقٍ وَأَخْرِجْنِي مُخْرَجَ صِدْقٍ وَاجْعَل لِّي مِن لَّدُنكَ سُلْطَانًا نَّصِيرًا
- ‏رَبِّ لَا تَذَرْنِي فَرْدًا وَأَنْتَ خَيْرُ الْوَارِثِينَ
- ‏رَّبِّ ارْحَمْهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرًا
- رَبِّ إِنِّي ظَلَمْتُ نَفْسِي فَاغْفِرْ لِي
- رَبِّ هَبْ لِي حُكْمًا وَأَلْحِقْنِي بِالصَّالِحِينَ
- رَبِّ اغْفِرْ لِي وَلِوَالِدَيَّ وَلِمَنْ دَخَلَ بَيْتِي مُؤْمِناً وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ
- ‏رَبِّ ابْنِ لِي عِندَكَ بَيْتًا فِي الْجَنَّةِ
- وَأُفَوِّضُ أَمْرِي إِلَى اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ
- لَّا إِلَٰهَ إِلَّا أَنتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ الظَّالِمِينَ
- رَبِّ إِنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ
- رَبَّنَا لَا تُزِغْ قُلُوبَنَا بَعْدَ إِذْ هَدَيْتَنَا وَهَبْ لَنَا مِن لَّدُنكَ رَحْمَةً ۚ إِنَّكَ أَنتَ الْوَهَّابُ
- رَبَّنَا آتِنَا مِن لَّدُنكَ رَحْمَةً وَهَيِّئْ لَنَا مِنْ أَمْرِنَا رَشَدًا
- ‏رَبَّنَا فَاغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرْ عَنَّا سَيِّئَاتِنَا
- رَبَّنَا آتِنَا فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الْآخِرَةِ حَسَنَةً
- رَبَّنَا لاَ تُؤَاخِذْنَا إِن نَّسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَا رَبَّنَا وَلاَ تَحْمِلْ عَلَيْنَا إِصْرًا كَمَا حَمَلْتَهُ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِنَا رَبَّنَا وَلاَ تُحَمِّلْنَا مَا لاَ طَاقَةَ لَنَا بِهِ وَاعْفُ عَنَّا وَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا أَنتَ مَوْلانَا

24/04/2026

ቁርአን ላይ ከተቀመጡ ታሪኮች ውስጥ ከሚገርሙኝ....የነብዩላህ ሙሳ love life!❤

ነብዩላህ ሙሳ, The big guy, the strong fit man፣ አንበሳው ከሀገራቸው አምባገነኑ የፊርአውንን መንግስት ሸሽተው ተሰደው ሲጓዙ መድየን ወደምትባል ቀበሌ ደረሱ። የቀበሌው ሰው ታዲያ መድየን ውስጥ ባለችዋ ብቸኛ የዉሀ ምንጭ እየተጋፋ ግመሉንና ፍየሉን ያጠጣል። ጉልበተኛ እዛ ነው የሚታየው በቃ። ያለችው ምንጭ አንድ ነች እዛ ተጋፍቶ የሚያጠጣውና ለራሱም የሚቀዳው አለ የተባለ ጠንካራ ወንድ ነው። የከተማው ወንድ ታዲያ ትግል የሚገጥመው እዛ ነው። ሁሉም ታግሎ ያጠጣል ይጠጣል። ከዛ ደካሞቹ ደግሞ ጉልበተኞቹ ታግለው አጠጥተው እስኪጨርሱ ዳር ላይ ተኮራምተው ይጠብቁና መጨረሻላይ በትግሉና በፍትጊያው የደፈረሰውን ውሀ እንስሳቶቻቸውንም ያጠጣሉ እነሱም ይጠጣሉ። ለቤታቸውም የደፈረሰውን ውሀ ይቀዳሉ። ታዲያ ምን ያርጉ💁

ነብዩላህ ሙሳ በስደት በረሀውን ተጉዘው መድየን ምንጭ ውሀ ሲደርሱ ሰዉ ይራኮታል። የጦፈ ትግል ነው ያለው። በዚ መሀል አሻግረው ሲያዩ ሁለት ሚስኪን ልጃገረዶች ጥግ ላይ ቆመው እንስሳቶቻቸውን ሰብሰብ አርገው ይጠብቃሉ። ሙሳ(አሰ) ሁኔታቸው ግራ ገባቸውና ተጠግተው ምነው እንስሳቶቻችሁን አታጠጡምን? ሲሉ ጠየቋቸው። እነሱም ምን እናርግ ብለህ ነው አቅም የለንም እዚ ተጋፍቶ ማጠጣት። አባታችንም ሽማግሌ ነው አቅም የለውም። ስለዚህ ጠብቀን ጉልቤዎቹ ሲጨርሱ እንጂ ማጠጣት አንችልም ሲሉ መለሱ። ሙሳም ነው እንዴ አሉና የልጆቹን ፍየሎች ይዘው ወደምንጩ በመሄድ ምንጩ ላይ ያለን ጉልቤ ሁሉ አተራመሱት። ለጉልቤም ጉልቤ አለው አሉ እትዬ ዙልፋ። ማን ይግፋቸው ሙሳን። እያንዳንዱን አሽቀንጥረው ጥለው የሴቶቹን ፍየሎች አጠጥተው ለራሳቸውም ጠጥተው ጉልቤውን ሁሉ ልክ አስገብተው ተመለሱና ፍየሎቹን ለሴቶቹ ሰተው ሂዱ በሉ ብለው እሳቸው ያው ስደተኛና ሙሳፊር ናቸውና መንገዳቸውን እስኪቀጥሉ ትንሽ ልረፍ ብለው ዛፍ ስር ቁጭ አሉ። ያላገቡ ላጤ የነበሩትና ስራም ቤትም መሄጂያም ማረፊያም ያልነበራቸው ስደተኛውና ሙሳፊሩ ነብዩላህ ሙሳ ዛፏ ስር ቁጭ ብለው َربِّ إِنِّي لِمَا أَنزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ" " ጌታዬ ሆይ እኔ አንተ ወደኔ ላወረድከው በጎ ነገር ከጃይ ነኝ" ሲሉ ዱአእ አደረጉ። እቺ ዱአእ ስንት ነገር መለሰች?እናየዋለን.... ግን እዚጋ ጀለሴ ለካ ከሴቶቹ አንደኛዋ እዛው wow ብላለች..ሁብ ጠብ አርጓታል። ሙሳ (አሰ) መች አወቁና

ሴቶቹ ቤታቸው እንደደረሱ በጊዜ መመለሳቸው ግራ የገባቸው አባታቸው ምነው ዛሬ ሲሉ ጠየቁ። ሴቶቹም ያጋጠማቸውን ይነግሯቸዋል። አባታቸውም ስማቸው ነብዩላህ ሹአይብ(አሰ) ይባላሉ። ደስ አላቸው ከዛም ጠርተው ሊያመሰግኑት እሺ ካለ ደግሞ ለሰራው ስራ ሊከፍሉት እንድትጠራው ከሁለቱ ልጆች መሀል ልቧ ጠብ ያለውን ልጅ ላኳት። እሳቸውም መች አወቁና። እየሮጠች ሄደች። ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ አገኘችው። አይኗን ሰበር አርጋ አባቷ እንደሚፈልጉት ነገረቻቸው። ሙሳም (አሰ) ጥሪ ማክበር ዋጂብ ነውና እሺ አሉ። እሳቸው ከፊት እሷ ከሗላ ሆነው መንገዱን እሳቸው አያውቁትምና መታጠፍ ሲኖርባቸው በድምፅ ሳይሆን መታጠፍ ወዳለባቸው አቅጣጫ ጠጠር እየወረወረች እየመራቻቸው ከፊትና ተጠባብቀው አባቷ ቤት ገቡ። ልጅቷ በሰውዬው አላህን መፍራት፣ ታማኝነት አይናፋርነትና ጀንትልነት ይባስ ማረካት። አባትየውም ተቀበሉት። አመሰገኑት። ከየት ነህ አሉት። ታሪኩን ሙሉ ነገራቸው። አላህ አትርፎሀል አይዞህ ሲሉ አፅናኑት። ሙሳም መቼስ መንገደኛ ነውና ዛሬን አድሮ ነገ ወደማያውቀው መንገድ መጓዙ አይ

 #ሰበር መረጃ፦ጉደኛዋ ኢራን ጉድ አፈላች! #ኢራን የተናገረችውን አደረገችው! #ኢራን ለክፉ ቀን ብላ ካስቀመጠቻቸውና አለም ካላያቸው መሳሪያዎቿ መካከል አንዱን ብቻ ወደ ሆርሙዝ አቅጣጫ ተኩ...
23/04/2026

#ሰበር መረጃ፦ጉደኛዋ ኢራን ጉድ አፈላች!
#ኢራን የተናገረችውን አደረገችው!
#ኢራን ለክፉ ቀን ብላ ካስቀመጠቻቸውና አለም ካላያቸው መሳሪያዎቿ መካከል አንዱን ብቻ ወደ ሆርሙዝ አቅጣጫ ተኩሳ አለምን ጉድ አሰኝታለች፣አሜሪካን እና እስራኤልን ደግሞ በድንጋጤ አመዳቸው ቡን አንዲል አድርጋለች።

ይቺ ለጉድ የፈጠራት የአሜሪካና የእስራኤል የጎን ውጋትና የሆድ ቁርጠት የሆነች ሀገር ለካ የምትፎክረውና የአለም አለቃ ለሆነችው አሜሪካ ጭምር አልታዘዝም ያለችው በፈጣሪዋና በመሳሪያዎቿ ተማምና ነው።

ኢራን አዲስ ይፋ ያደረገችውና ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ ያስወነጨፈችው አዲሱ የጦር መሳሪያ "የመሳሪዎች ንጉስ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ሲተኮስ ከአፈሙዙ ሲወጣ አኖድ ሆኖ ይወጣና ዐየር ላይ ተጉዞ ኢላማው ጋር ሲደርስ እዛው ዐየር ላይ በመፈንዳት በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ፈንጂዎችን ወደ ሰማይ በመልቀቅና በመንጋ ወደሚፈለገው ኢላማ ሄደው እንዲፈነዱ የሚያደርግ ነው።

በእርግጥም ኢራን የሰላም ድርድሩ ካልተሳካና አሜሪካ ዳግም ኢራን ላይ ወረራ ከፈፀመች ምላሹ የከፋ ይሆናል።አለም አይቷቸው የማያውቃቸውን መሳሪያዎች ይፋ አደሮጋለሁ ስትል የነበረው ዛቻ እውነት መሆኑን የዚህ አዲስና አደገኛ መሳሪያ ይፋ መሆን ጥሩ ማስረጃ ነው።

ኢራን አሁንም ገና ያልተነኩና ያልታዩ አዳዲስ መሳሪያዎች አሉኝ።ኢራን በምንም አይነት መመዘኛ በአሜሪካና በእስራኤል አትሸነፍም።ነፃነቷንና ሉኣላዊነቷን አስከብራ ትኖራለች ሲሉም የሀገሪቱ ባለ ስልጣናት ጠንከር ያለ አቋማቸውን ገልጸዋል።

የተኩስ አቁሙ ስምምነት ሊጠናቀቅ ጥቂት ሰዓታት በቀሩት በዚህ ወቅት ኢራን ይህንን አዲስና አውዳሚ መሳሪያ ይፋ ማድረጓ የቀጠናውን ውጥረት ወደ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሮታል።

23/04/2026

ምርጫውን ከሚያሸንፈው ፓርቲ ይልቅ ፕሪሚየም ሊጉን የሚያሸንፈው ቡድን የሚያሳስበው ትውልድ😑

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hanan Taha posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share