አቡበክር ጎንደር የሃበሻ ልብስ አቅራቢ/ Abuboker habesh clothing center Gondar

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • አቡበክር ጎንደር የሃበሻ ልብስ አቅራቢ/ Abuboker habesh clothing center Gondar

አቡበክር ጎንደር የሃበሻ ልብስ አቅራቢ/ Abuboker habesh clothing center Gondar አቡበክር የተለያዩ ፋሽን የሀበሻ ቀሚስ የወንዶች ኮት በጥራት

16/03/2026
16/03/2026

1. "ድህነት ወንጀል አይደለም፣ ነገር ግን በጣም አስቸጋሪ የሆነ ቅጣት ነው።"
2. "ከሌላ ሰው ገንዘብ ተበድረህ ሀብታም ለመምሰል አትሞክር፤ ምክንያቱም ያበደረህ ሰውዬ ሲያይህ የራሱን ብልጽግና እንጂ ያንተን ስኬት አይመለከትም።"
3. "አልጋህ ላይ ተኝተህ ጸሎት ብቻ በማድረግ ሚሊየነር መሆን አትችልም። እግዚአብሔር አብርሃምን 'ሂድ' ነው ያለው እንጂ 'ተኛ' አላለውም።"
4. "ዲግሪ መያዝ ብቻውን ስኬት አይደለም። ዲግሪው በኪስህ ሆኖ ጭንቅላትህ ባዶ ከሆነ፣ ያ ዲግሪ የአምስት ደቂቃ ኩራት ብቻ ነው የሚሰጥህ።"
5. "እድል ማለት ዝግጅት እና አጋጣሚ ሲገናኙ ነው። ዝግጁ ካልሆንክ እድሉ መጥቶ ሲያንኳኳ አንተ ተኝተህ ይሆናል።" 6. "መሪ መሆን ማለት ሰዎችን ማዘዝ ብቻ አይደለም፤ ሰዎቹ ወዴት መሄድ እንዳለባቸው ማሳየትም ጭምር ነው።" የሙጋቤ "የገንዘብ ፍልስፍና" ማጠቃለያ ሙጋቤ ብዙ ጊዜ አፍሪካውያን በራሳቸው ሀብትና ንብረት ላይ እንዲተማመኑ ይወተውቱ ነበር። የምዕራባውያንን እርዳታ ከመጠባበቅ ይልቅ "የራሳችሁን መሬት እረሱ፣ የራሳችሁን ስራ ፍጠሩ" የሚል ጠንከር ያለ መልዕክት ነበራቸው። በነገራችን ላይ በሙጋቤ ዘመን ዚምባብዌ ከፍተኛ የገንዘብ ግሽበት (Inflation) አስተናግዳለች። ይህ ደግሞ ብዙ ሰዎች በሳቸው ስም ስለ ገንዘብ የሚቀለዱባቸው ቀልዶች እንዲበራከቱ ምክንያት ሆኗል። ሙጋቤ ራሳቸው ሰባት ዲግሪዎች የነበሯቸው ምሁር ነበሩ። ስለዚህ ስለ ትምህርት ያላቸው አመለካከት ጥልቅና አንዳንዴም ተሳላቂ ነበር።
7. "ትምህርት ማለት አእምሮህን በሌሎች ሰዎች ሀሳብ መሙላት ብቻ አይደለም፤ ያንን ሀሳብ ተጠቅመህ የራስህን ዓለም መለወጥ መቻል ነው።"
8. "ፈተና ላይ የምታገኘው ውጤት የወደፊት ህይወትህን አይወስነውም፤ ነገር ግን በትምህርት ቤት ያሳየኸው ስነ-ምግባር ማንነትህን ይገልጻል።"
9. "ብዙ ዲግሪ ኖሮህ በሀገርህ ውስጥ ያለውን ችግር መፍታት ካልቻልክ፣ ዲግሪህ ለቤትህ ግድግዳ ጌጥነት ብቻ ነው የሚያገለግለው።" ሙጋቤ የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነትን ክፉኛ የሚቃወሙና አፍሪካውያን በራሳቸው እንዲቆሙ የሚወተወቱ መሪ ነበሩ።
10. "አፍሪካ ለአፍሪካውያን ናት! የእኛን መሬትና ሀብት እንዴት እንደምንጠቀምበት ሌላ ሰው እንዲነግረን አንፈልግም።" 11. "ነፃነት ማለት ባንዲራ መቀየር ብቻ አይደለም፤ የሀገርህን ኢኮኖሚና የወደፊት እጣ ፈንታ በእጅህ ማስገባት ማለት ነው።"
12. "አፍሪካውያን ካልተባበርን፣ እንደ ግለሰብ ተራ በተራ እንሰበራለን። እንደ ዱላ ስብስብ ከታሰርን ግን ማንም ሊሰብረን አይችልም።" የሙጋቤ ታሪካዊ አሻራ ሮበርት ሙጋቤ በዚምባብዌ ታሪክ ውስጥ ሁለት መልክ ያላቸው መሪ ተደርገው ይታያሉ፦ * እንደ ነፃነት ታጋይ (Liberator): ሀገራቸውን ከነጭ አናሳ አገዛዝ ነፃ ያወጡ ጀግና። * እንደ አምባገነን (Dictator): ለረጅም ዓመታት ስልጣን ላይ በመቆየታቸውና በኢኮኖሚ ውድቀት የሚወቀሱ። ማጠቃለያ የሙጋቤ ንግግሮች ሁልጊዜም ኩራትን (Pride)፣ ተቃውሞን (Resistance) እና ቀልድን (Wit) ያቀላቀሉ ናቸው። ሰዎች በፖለቲካቸው ቢስማሙም ባይስማሙም፣ ንግግራቸው ግን ለረጅም ጊዜ ሲታወስ ይኖራል። የቱ ተመቻችሁ

#ሼር

08/03/2026

ምናልባት እኝህንም ሰዎች ቤት ሲገቡ ሚስቶቻቸው "አንተ ምን አለብህ ከልጆቹ ጋር ስዳረቅ የምውለው እኔ" ትላቸው ይሆናል እኮ😞

21/02/2026
19/02/2026

የአፍሪካው ቁጥር አንድ ቢሊየነር ግዙፍ
ኢምፓየራቸውን ለሶስት ሴት ልጆቻቸው አስረከቡ!

የአፍሪካ ባለጸጋው አሊኮ ዳንጎቴ፣ የዳንጎቴ ግሩፕን የወደፊት እጣ ፈንታ እና አለምአቀፍ ተስፋፊነት ለማረጋገጥ ሶስቱን ሴት ልጆቻቸውን በከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ መሾማቸውን አስታውቀዋል። ይህ ታሪካዊ እርምጃ የድርጅቱን ተተኪ አመራር የማዘጋጀት እና አለምአቀፋዊ ተወዳዳሪነቱን የማሳደግ ስትራቴጂ አካል ተደርጎ ተወስዷል።

በሹመቱ መሰረት፣ ሀሊማ አሊኮ ዳንጎቴ የዳንጎቴ ቤተሰብ ቢሮን እና አለምአቀፍ ቢሮዎችን እንድትመራ የተመደበች ሲሆን፣ በተለይም በዱባይ የሚገኙ የድርጅቱን ቅርንጫፎች በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና ትጫወታለች። ፋጢማ አሊኮ ዳንጎቴ በበኩሏ የነዳጅ እና ጋዝ ዘርፉን በበላይነት እንድትመራ የተመደበች ሲሆን፣ ግዙፉን የነዳጅ ማጣሪያ እና የፔትሮኬሚካል ስራዎችን ጨምሮ ቁልፍ የድርጅት ተግባራትን ታስተዳድራለች።

በተጨማሪም ማሪያ አሊኮ ዳንጎቴ የሲሚንቶ እና የምግብ ምርቶች የንግድ ስራዎችን እንድትመራ ኃላፊነት ተሰጥቷታል። ማሪያ በዋናነት የገበያ እድገት እና የአሰራር ጥራትን በማረጋገጥ ላይ ትኩረት አድርጋ እንደምትሰራ ተገልጿል። ይህ ሹመት ዳንጎቴ ግሩፕን ወደ አዲስ ከፍታ ለማውጣትና በቤተሰብ አባላት መካከል ያለውን የስልጣን ሽግግር ስርአት ለማጠናከር የተወሰደ ደፋር እርምጃ ነው።

Via:- AdissAdmas

25/01/2026

የቴዲ አፍሮ የሰርግ ሪከርድ ተሰበረ!

320,000,000 million Birr የወጣበትና በኢትዮጵያ ታሪክ የዘመናዊ ሽምግልና የመጀመሪያው ውድና በአቀራርቡ ልዩ የሆነው የሰርግ ስነ ስርዓት በውቢቷ አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ በዚህ ቀን ተካሄደ።

12 ብዛት ያላቸው የአስር ሚሊዮን ብር ዋጋ የያዙ 12 ቸኮች(cheques) የ32 million birr መኪና እና 4,400,000 birr አልባሳትና 4,090,000 birr ግምት ያላቸው ወርቆችና 4,145,000 birr ዳይመንድ ቀለበና አጠቃላይ የ320 million birr ሰርግ።

ለሙሽሪት ከተዘጋጁት ስጦታዎች መካከል በልዩ ሁኔታ ያጌጠ እና ሙሉ የቤትና የግል መገልገያ ስጦታዎችን የያዘ ተሽከርካሪ፣ ብራንድ የሆኑ ዘመናዊ ሻንጣዎች የሞሉት ልብስ፣ ሽቶዎች እንዲሁም እጅግ ውድ የሆኑ ሙሉ የወርቅ ጌጣጌጦች ተበርክተውላታል።

ይህ "የአቤል እና የዓብስራ" ጥሎሽ በከተማው ካየናቸው ውድና የቅንጦት የጥሎሽ ስጦታዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ ሆኗል።

በነገራችን ላይ ሀገር ድሀ ምትሆነው በገንዘብ (capital) ማነስ ብቻ አደለም። የሀገሪቱ ገንዘብ በተወሰኑ ሰዎች እጅ ላይ ሲገኝ ነው። ግዮን ማለዳ ለሙሽሮቹ መልካም የትዳር ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል!

ከስር ያለውን የቴሌግራም ቻናላችንን አሁኑኑ join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ ሊንኩን ይጫኑ 👇

https://t.me/GhionMaleda

07/09/2025

አንድ የአረብ ልዑል ለትምህርት ወደ እንግሊዝ አገር ሄደና ከአንድ ወር በኋላ ለአባቱ መልዕክት ላከለት

"አባዬ ለንደን ቆንጆ ከተማ ናት ሰዎቹም በጣም ጥሩዎች ናቸው
እኔ ግን በአንድ ነገር እያፈርኩኝ ሀዘን እየተሰማኝ ነው
እሱም ሁልጊዜ ከምኖርበት ቤት ተነስቼ ዩኒቨርስቲ በር ላይ ደርሼ ከቅንጡ ውድ መኪናዬ ላይ ስወርድ የእኔ ታላላቅ ፕሮፌሰር አስተማሪዎቼ ከባቡር ላይ ነው የሚወርዱት"

ከቀናት በኋላ ልጁ ከአባትየው የተላከ መልዕክት ደርሶት ሲያነበው
"ልጄ በሰው አገር አፍረህ እኔንም አታሳፍረኝ በባንክ አካውንትህ ገንዘብ ልኬልሀለሁ እና ባቡሩን ግዝተህ ተመላለስበት" 😎

26/08/2025

Radric Davis ( ጉቺ ሜን ) አሜሪካዊ ራፐር ነው ። ከጎኑ ያለችው ደሞ Keyshia Ka'Oir ትባላለች ፡ ሞዴሊስት ፡ ጎበዝ አክትረስና ፡ ኢንተርፕረነር ነች ። ይለናል Wasihune Tesfaye

እና ፡ ከአመታት በፊት ፍቅረኛዋ ጉቺ ሜን ፡ በአንድ ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀረበና ፡ የሶስት አመት እስር ተፈረደበት ።....
ጉቺ ሜን ፡ ይህን የዳኞቹን ውሳኔ እንደሰማም ፡ ፍቅረኛውን ኬይሽያን ፡ ወደ እስር ቤት እንድትመጣ ላከባት ። ...
እየውልሽ ፡ በእስር ቤት ቆይታ ምን እንደሚፈጠር አላውቅም ። ስለዚህ በስሜ ያለውን ሁለት ሚሊየን ዶላር ፡ ወደ አንቺ ባንክ አካውንት እንዲዛወር እፈልጋለሁ አላት ።..
እና በባንክ ያለውን ብር በሙሉ ፡ አንድም ሳያስቀር ፡ ለፍቅረኛው ኬይሽያ ሰጣት ።
ጓደኞቹ ቀለዱበት ። ታስረህ ስትፈታ ጎዳና ልትወድቅ ነው ? ይህን ሁሉ አመት ትጠብቀኛለች ብለህ አታስብ አሉት ። ....
Keyshia Ka'Oir ፍቅረኛዋ የሰጣትን ገንዘብ ከባንክ ያወጣችው ብዙም ሳይቆይ ነበር ። እናም በገንዘቡ የራሷን Ka'Oir የሚባል የኮስሞቲክስ ማምረቻ ከፍታ መንቀሳቀስ ጀመረች ።...
ጊዜው ሳይታወቅ ሄዶ ፡ ፍርደኛው ራፐር ጉቺ ሜን የእስር ጊዜውን ጨርሶ ወጣ ። ጓደኛው ኬይሺያ ፡ በስራ ምክንያት ቢዚ ብትሆንም ፡ አልፎ አልፎ እየመጣች ትጠይቀው ነበር ። እና እንደተፈታ በዘመናዊ መኪና መጥታ ፡ ወደ አዲስ ቤት ይዛው ሄደች ። ከዚህ ሁሉ አመት መለያየት በኋላ ትጠብቀኛለች ብሎ ባያስብም ፡ እሷ ግን ከአመታት በኋላም ሳትቀየር ነበር ያገኛት ።

እና ቤት ደርሰው አረፍ ካሉ በኋላ ፡
" ጉቺ እስር ቤት ስትገባ ፡ በወቅቱ ሚስትህ ሳልሆን ፡ ትክደኛለች ሳትል ፡ ሁለት ሚሊየን ዶላር ሰጠኸኝ ነበር አይደል ? " አለችው ።
አዎ አላት ።
ይኸው ስድስት ሚሊየን ዶላር ሆኖ ጠብቆሀል አለችና ፡ የባንክ ቡኳን እንዲያየው ሰጠችው ።....
ዛሬ ላይ ፡ ጉቺ ሜን ፡ ከዛች ፍቅሩን ብቻ ሳይሆን የሰጣትንም ገንዘብ በእጥፍ አሳድጋ ከጠበቀችው Keyshia Ka'Oir ፡ ጋር ተጋብተው ፡ ትዳራቸው በልጅ ደምቆ , አብረው ይኖራሉ ።....
መታመን !

05/08/2025
24/07/2025

ሥራን ሳትደክም እንዴት ልትሠራ ትችላለህ?

ዳንኤል ጆሳለን እንዲህ ሲል ተናግሯል " ምን ያህል እንደሠራሁ የምለው በድካሜ መጠን ሳይሆን ባለመድከሜ ነው ፤ የዕለት ተግባርን አከናውኜ እንዳበቃሁ በተለየ ሁኔታ ከደከመኝ ወይም ቁጣ ቁጣ ካለኝ አዕምሮዬ እንደተዳከመ እረዳለሁ።

በዚህም ያን ዕለትም ያለምንም ጥያቄ በጥራትም ሆነ በብዛት ጥሩ ሥራ ያልሠራሁበት ቀን መሆኑን እገነዘባለሁ" ይላል።

ስለዚህ ወዳጄ የዕለት ተግባርህን አከናውነህ እንዳበቃህ ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ...

ምን ያህል ነው የደከመኝ ?

የሠራሁት የአዕምሮ ሥራ አድክሞኛል ወይስ የሠራሁበት መንገድ ነው ያደከመኝ?

እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ የምትችል ከሆነ ብዙ ሥራን በትንሽ ድካም መሥራት እንደምትችል ይገባልሃል።

ለምትሠራው ሥራ ክብር እና ፍቅር ይኑርህ እንጂ በፍፁም አክብደህ አትመልከተው ይህም ሥራህን ሳትደክም እንድትሠራው ይረዳሃል።

ሥራህን ሥትሠራ በተዝናና ስሜት ውስጥ ሆነህ ለመሥራት መሞከር አለብህ።

መልካም ቀን!!

Address

Gondar

Telephone

+251934513090

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አቡበክር ጎንደር የሃበሻ ልብስ አቅራቢ/ Abuboker habesh clothing center Gondar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share