Ze boloso green page

Ze boloso green page Ze boloso green page, Fashion, Itabashi-kuの連絡先情報、マップ、方向、お問い合わせフォーム、営業時間、サービス、評価、写真、動画、お知らせ。

10/02/2023

የዶ/ር ወዳጄነህ መልዕክት

| እኔማ የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን የማውቃት ይመስለኝ ነበር። ባለፉት ሦስት ቀናት እንደተረዳሁት ግን ስላንቺ የነገሩኝ ሰዎችና መጻህፍት ሁሉ ካለሽ ክብር፣ ሞገስና ዝና ከፊሉን እንኳን እንዳልነገሩኝ ነው።

ተዋህዶ ሆይ!

ንፁህ እምባ፣ ጥልቅ ትህትና፣ ብርቱ ትዕግስት፣ ታላቅ ጥበብ፣ ብዙ እውቀት፣ ሰፊ ማስተዋል፣ የሚያስፈራ ግርማ አየሁብሽና ተገረምኩኝ፣ ልቤ ተደነቀ፣ እጄን በአፌ ላይ ጫንኩኝ! የጸሎትና የምልጃሽ እጣን የልዑል እግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ሲያጥነው፣ ዙፋኑን ሲያውደው ማየት እንኳን እኔን ደካማውን ሰው ይቅርና ቅዱሳን መላዕክቱን ያስደንቃል።

በነቢዩ በዳንኤል መፅሃፍ እንደሚነበብ እጅ ያልነካው ድንጋይ ከሰማይ ወርዶ ሳይፈርስ ፣ ሳይከፈል፣ ሳይቆረስ ታላቅ ተራራ ሆኖ ጸንቶ እንደኖረ አንቺም በኢትዮጵያ ምድር ላይ ታላቅ ተራራ ሆነሽ ለአፍሪካ ትምክህት፣ ለመላው አለምም ክብር ሆነሽ ትኖሪያለሽ።

ከእግዚአብሔር የተማሩት፣ ትሁታንና ብሩካን የሆኑት፣ ማቅ የለበሱልሽ የተወደዱ ልጆችሽ እንዴት የታደሉ ናቸው!

ከሩቅ እያየሽ የሚወድሽና የሚያከብርሽ

ዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ

05/02/2023

አርቲስት ንጹህ ሀይሌ

ፈጣሪ ከተጐዱ ወገኖች ጋር ነው ሁሉም ያልፏል
04/02/2023

ፈጣሪ ከተጐዱ ወገኖች ጋር ነው ሁሉም ያልፏል

ብፁዕ አቡነ ያሬድ በአሰላ መቆየት አይችሉም ተብለው በዚህ ሰዓት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርገዋል።

18/01/2023

ስለኢየሱስ ከእኛ ሰምተው ...እኛን ይከሱናል!
***

ማን ነው ኢየሱስን የመሰለው? ማን ነው ኢየሱስን ያከበረው?

የማምለኪያ ህንጻ መቅደሶቻችንን ኢየሱስ፣አማኑኤል፣መድኃኒዓለም ብሎ ሰይሞ ስሙን አምልኮ ስሙን የሚያስበው ማን ነው??

ከጽንሰቱ እስከ ትንሣኤው በዓል አውጃ ስሙን ያከበረችው የትኛዋ መቅደስ ናት?

መጠመቁን አስባ ጥምቀትን በዓል ያደረገችው መቅደስ የትኛዋ ናት?

ጌታዬ መድኃኒቴ ብላ ከስሙ በፊት የጌትነትን እና የመድኃኒትነት አዋጅ አውጃ የምትጠራው የትኛዋ መቅደስ ናት ?

ለስሙ ቅዳሴ ቀምራ፣ቅኔ ተቀኝታ ፣ማህሌት ቆማ" ኢየሱስ " ከሚለው ስም ጋር ሌት ተቀን በፍቅር የወደቀችው የትኛዋ መቅደስ ናት?

ሥጋውን መብላት ደሙን መጠጣት የዘለዓለም ህይወት እንዳለው ሰብካ እና ስርዓት ዘርግታ ከሥጋ እና ደሙ ጸጋ ብርሃንን እናገኝ ዘንድ የምታቆርበን የትኛዋ መቅደስ ናት?

ሁሉንም መርኃግብራትን እሱ እንዳስተማረው ...አሜን አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር...ብላ የጸሎቶች ሁሉ ቁንጮ እና ምንጭ አድርጋ የኖረችው የትኛዋ መቅደስ ናት ?

መርኃግብራቷን ስትጨርስ "እግዚኦ መሐርና ክርስቶስ" ብላ የክርስቶስን ምህረት ቸርነት የምትማጸን መቅደስ የትኛዋ ናት?

ወደ እውነት የሚወስደን አማናዊ መንገድ፣ ህይወት የምናገኝበት እርሱ እራሱ ህይወት የሆነ ንጉስ መሆኑን ተቀብላ "የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ" የምትለው መቅደስ የትኛዋ ናት?

የቆመችበት መሰረት፣የምትገለጥባት ጉልላት የእርሱ ስም እና ክብር የሆነላት መቅደስ የትኛዋ ናት?

ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ መቅደስ አይደለችምን?

አማናዊውን ኢየሱስ እመን ...ተጠመቅ ። ትድናለህ

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

28/09/2020

If the interested civil engineers can join us

30/06/2016

住所

Itabashi-ku, Tokyo

ウェブサイト

アラート

Ze boloso green pageがニュースとプロモを投稿した時に最初に知って当社にメールを送信する最初の人になりましょう。あなたのメールアドレスはその他の目的には使用されず、いつでもサブスクリプションを解除することができます。

ショートカット

共有する

カテゴリー