Alem Tibeb - Ethiopia traditional clothes +251946603650

Alem Tibeb -  Ethiopia traditional clothes +251946603650 የባህል አልባሳትን በትዕዛsዝ እንሰራለን
0946603650

25/11/2023
21/11/2023

Check out Alem Birhanie's video.

18/11/2023

😭😭

#ይህ የ 5 አመት ህፃን ይባላል ሰኞ ህዳር 3 እቤት የመጣ እንግዳ ወክ አድርገን በቶሎ እንምጣ ብሎ

#ከዝዋይ አለም ጤና አካባቢ አብረው ወጥተው በዛው ቀርተዋል እናትና አባት ለቀናት ለቅሶና መንከራተት ላይ ናቸው እባካችሁን #ሼር በማድረግ አንጀት የሚበላውን ህፃን እንፈልገው

#ስልክ ቁጥር

09 10 74 11 06

09 78 05 06 04

#ሰውን ለመርዳት ትክክለኛው ጊዜ #አሁን ነው !!

#ዮናስ ደምሴ ( የአይንዬ ልጅ )

11/10/2023

ህፃን #አቤል የት ነው? ማን ሰወረው?
ሼር በማድረግ እናፋልግ

አንዲት ስራ የሌላት ምስኪን እናት በቲቪ መስኮት እስራኤል ዳንሳ "ጨለማ የሆነባችሁ ሁሉ ብርሀን ይሆንላችኋል፣ የጨነቃችሁም ችግራችሁ ይፈታል" ሲል ሰምታ "ችግሬ ከተወገደልኝ ስራም ካገኘሁ" በሚል ተስፋ የ8ዓመት ልጇን ይዛ ከሰበታ ወደ አዲስአበባ ትመጣለች!!

ማክሰኞ መስከረም8 22አክሱም ሆቴል ጎን የሚገኘው እስራኤል ዳንሳ ቸርች ገብታ ከ4:30 ጀምሮ ፕሮግራም እየተከታተለች ፊት ለፊቷ ሲጫወትና ከቦታቦታ ሲዞር የነበረው ትንሹ አቤል 8:30አካባቢ ድንገት ይጠፋባታል!መድረክ ላይ ብታስነግር ሰዎችንም ስትጠይቅ "አየነው"የሚል ሰው ታጣለች!

በሰዓቱ ሀይለኛ ዝናብ እየዘነበ የግቢውም በር የተዘጋ ስለነበር "ወደ ውጪ አይወጣም"የምትለው እናት ወደ ጥበቃዎቹ ተጠግታ "እረ ልጄ ጠፋብኝ አይታችሁታል ወይ"ስትላቸው"አንድ ጥበቃ "አላየነውም ልጅሽ ግን ጥሩ ጭንቅላት አለው፣ ምንም አይሆንም፣ከ4ቀን በኋላ ይመለሳል፣ ከእግዚአብሔር ጋር ተገናኚ፣ፀሎትም አድርጊ"ይላታል!!

እናት አበባ ውጪ አልጋ ይዛ እያደረች በየቀኑ ወደ ቸርችና ፖሊስጣቢያ እየተመላለሰች ከ20ቀናት በላይ ልጇን በተስፋ ብትጠብቀም እስካሁን የት እንዳለ አላወቀችም!እስራኤል ዳንሳን ለማግኘትና የሆነውን ለመንገር ብትሞክርም ወደሱ የሚያቀርባት ሰው አላገኘችም!
ህፃን #አቤል ምንድነው የሆነው?የትስ ነው ያለው??
በጉባኤው የነበረው ሰው ይዞት ሄዶ ነው?ከግቢ ወጥቶ ጠፍቶ ነው?ወይስ ጥበቃው የሚያውቀው ነገር አለ?
እናት እንቆቅልሽ ሆኖባታል! 22ቀናት በእንባና በፍለጋ እየተንከራተተች ነው! እናንተ ደጋጎች እባካችሁን #ሼር በማድረግ እናግዛት🙏ልጇ በደህና እንዲገኝላት #በፀሎት እናስባት🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

0923699761-አበባ ረታ(እናት)
0962914796-ሙሊታ

08/10/2023
06/10/2023

38K likes, 914 comments. “ # 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ኢትዮጵያንቲክቶክ #ጳጳሳት 🇪🇹🇪🇹🇪🇹ኩራቴ😘ኢትዮ #ስልጤ ...

05/10/2023

‼️

ይህች ቆንጅዬ ህፃን ከየት እንደመጣች ባይታወቅም አሁን የምትገኘው ኮልፌ አጠናተራ አካባቢ ነው!! ይሄኔ እናት በፍለጋ እየተንከራተተች ነውና እባካችሁን #ሼር በማድረግ ቤተሰቦቿን እንፈልግ🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

0913559051-ጌቱ

12/09/2023



የ"ዕንቁጣጣሽ" አመጣጥ በአጭሩ

ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡

ሁለተኛው የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡ ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡ ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡
አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡
የዘመን ባለቤት የድንግል ልጅ መልካም ዘመን ያድርግልን የደስታና የተስፋ ዘመን የሆነች እመቤታችን ዘመኑን ትባርክልን:: አሜን🙏💖
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻 መልካም 🌻🌻️
🌻🌻 አዲስ 🌻🌻
🌻🌻 ዓመት 🌻🌻️
🌻️🌹⁣🌾🌻💐🌷🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊

Address

Shiro Meda
Addis Ababa

Telephone

+251946603650

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alem Tibeb - Ethiopia traditional clothes +251946603650 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share