Akaki kality woreda 8 prosperity party youths league - ብልጽግና

Akaki kality woreda 8 prosperity party youths league - ብልጽግና Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Akaki kality woreda 8 prosperity party youths league - ብልጽግና, Women's clothes shop, Addis Ababa.

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በየመሰረታዊ ድርጅት ዉስጥ ከሚገኙ ሙስሊም ወንድምና እህቶች ጋር አፍጥር መርሀ ግብር ማካሄድ ጀመረ::በቀን 06/072016 ዓ...
15/03/2024

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በየመሰረታዊ ድርጅት ዉስጥ ከሚገኙ ሙስሊም ወንድምና እህቶች ጋር አፍጥር መርሀ ግብር ማካሄድ ጀመረ::
በቀን 06/072016 ዓ.ም በተደረገዉ የአፍጥር መረሀ ግብር የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ብልፅግና ወጣቶች ሊግ ፅ/ቤት ኃላፊ ወጣት ማቲያስ ጌታቸዉ የተገኙ ሲሆን ይህ የአፍጥር መርሀ ግብር ወድማማችነትንና እህትማማችን ከመፍጠሩ ባሻገር ጠንካራ ተቋምን የሚፈጥር በመሆኑ በሌሎች ወረዳዎችም መስፋት አለበት በማለት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል። በተጨማሪም የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ብልፅግና ወጣቶች ሊግ ሰብሳቢ የሆኑት ወጣት ተማረ አየነዉ ይህ የአፍጥር መርሀ ግብር በወጣት ያሲን ቤት ይጀመር እንጅ በሁሉም መሰረታዊ ድርጅቶች ተጠናክሮ የሚቀጥል ነዉ ብለዋል።

 #ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ለተሻለ ዉጤት!በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 08  የብልፅግና ፓርቲ  ወጣቶች ሊግ  የመደመር ትውልድ መሰረታዊ ድርጅት አመራሮች እና ስራ አስፈፃሚዎች እስካ...
14/03/2024

#ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ለተሻለ ዉጤት!

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የመደመር ትውልድ መሰረታዊ ድርጅት አመራሮች እና ስራ አስፈፃሚዎች እስካሁን የተሰሩ ስራዎች ዙሪያና በቀጣይ በሚደረገው የአባላት ኮንፍረንስ ዙሪያ ውይይት አደረጉ።
******************************************************************
መጋቢት 5/2016 ዓ.ም

የአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 08 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የመደመር ትውልድ መሰረታዊ ድርጅት አመራሮችና ስራ አስፈጻሚዎች እስካሁን የተሰሩ መደበኛና ወቅታዊ ተግባራት የተመራበት አግባብና የተመዘገቡ ዉጤቶችን በጋራ የገመገሙ ሲሆን።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ኃላፊ ወጣት ማቲያስ ጌታቸው በሀገራችንም ሆነ በከተማችን ለተመዘገቡና እየተመዘገቡ ላሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የወጣቱ ሚና የላቀ መሆኑን ገልፀው ዘላቂነት ያለው ክትትልና ድጋፍ ተቋማትን ለማጠናከር የጎላ ሚና እንዳለውና ዛሬ እዚህ የተገኛችሁ የመደመር ትውልድ መሰረታዊ ድርጅት አመራሮች በእናንተ ስር ያሉ ህዋሳትንና አባላትን በመደገፍና በማብቃት መደበኛና ወቅታዊ ተልዕኮችን በሙሉ አቅም መፈፀም እንደሚያስፈልግ አስገንዝበው በቀጣይ ቀናት ቅዳሜና እሁድ ለሚካሄደው የአባላት ኮንፍረንስ በልዩ ትኩረት መሰራት እንዳለበት አሳስቧል ።

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የብልፅግና ፓርቲ ወጣት ሊግ ሀላፊ ወጣት ተማረ አየነው በዚህ ልክ የተሰሩ ስራዎችን እና በቀጣይ የሚደረጉ መድረኮችን በጋራ መገምገማችን የተሻለ ውጤት እንድናመጣና ለሌሎችም አቅም እንድንፈጥር የሚያግዝ መድረክ መሆኑን አስገንዝበው በቀጣይ ቅዳሜና እሁድ ለሚደረገው ኮንፍረንስ ልዩ ትኩረት ያስፈልገዋል ብሏል።

 #"የሚያስብ አዕምሮ እና የሚሰራ እጅ ይዘን ስራ የሚፈታ ጉልበት አይኖርም"በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በወረዳ 8 አስተዳደር በወረዳው ካሉ ስራ ፈላጊ ወጣቶችና ሴቶች ጋር "የ3 ወራት የወጣቶችና...
15/02/2024

#"የሚያስብ አዕምሮ እና የሚሰራ እጅ ይዘን ስራ የሚፈታ ጉልበት አይኖርም"

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በወረዳ 8 አስተዳደር በወረዳው ካሉ ስራ ፈላጊ ወጣቶችና ሴቶች ጋር "የ3 ወራት የወጣቶችና የሴቶች የስራ እድል ፈጠራ ንቅናቄ ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ለስራ የተነሳሱ የወጣቶችና ሴቶች ይዘን ድህነትን እንቀንሳለን" በሚል ሀሳብ በአንድ ማዕከል በወረዳ ደረጃ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የካቲት 7/2016 ዓ.ም

"እኔ ለሀገሬ  የሰላም ዘብ ነኝ"በአቃቂ ቃሊቲ  ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 "እኔ የሀገሬ  የሰላም ዘብ ነኝ" በሚል መነሻ ሀሳብ ከወረዳው ወጣቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።**********...
04/02/2024

"እኔ ለሀገሬ የሰላም ዘብ ነኝ"

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 "እኔ የሀገሬ የሰላም ዘብ ነኝ" በሚል መነሻ ሀሳብ ከወረዳው ወጣቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።
******************************************************
ጥር 26/2016 ዓ.ም

በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይናለም ግርማ እንደተናገሩት ወጣቶች የነገ ሀገር ተረካቢ እንደመሆናቸው መጠን በሀገር ደረጃ የሚሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ከወጣቱ ጋር ተቀናጅቶ መስራት ተገቢ መሆኑን ገልፀው፤ ወጣቱ የሀገሩን ሰላም በማስጠበቅ ለሰላም ዘብ መቆም እንደሚገባው አሳስበዋል።

የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት የወረዳ 8 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ሰብሳቢ ወጣት ተማረ አየነው በበኩላቸው ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ መስራት የሚቻለው ሰላም ሲኖር በመሆኑ ሁሉም አካል የራሱን የወረዳውን ብሎም የሀገሩን ሰላም ማስጠበቅ ላይ ግንባር ቀደም በመሆን መስራት እንደሚገባው ተናግረዋል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 8 ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ተመስገን ውድዬ ወጣቱ ለሰላም ዘብ በመቆም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣና ከኢኮኖሚ አንፃር የወጣቶች ቁልፍ ጥያቄ የስራ ዕድል ፈጠራ እንደሆነ እና ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የወጣቶችን የስራ አጥነት ችግር ለመፍታት በተደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረት የተመዘገቡ ስኬቶች እንደተጠበቁ ሆነው አሁንም የሀገራችን ወጣቶች አንገብጋቢ ችግር ስራ አጥነት መሆኑን ገልፀው ወጣቶች ስራ ሳያማርጡ ለዘላቂ ስኬት ወጣትነት በአካልና በአዕምሮ የጎለበተ ሀይል ዛሬን ዝቅ ብለን በመስራት የነገውን ስኬት የምንወስንበት በመሆኑ ለሁሉም ነገር በየብሎካችንና በያለንበት ለሰላማችን ግንባር ቀደም ሆነን መገኘት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በመድረኩም ላይ ከተሳታፊዎች ሀሳብና ጥያቄ የተነሳ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

"እኔ ለሀገሬ የሰላም ዘብ ነኝ" የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በክ/ከተማው ውስጥ ከሚገኙ ከሁሉም ወረዳዎች ከተውጣጡ የብልጽግና ፓርቲ ወጣት ሊግ አባላትና ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች ጋር ...
28/01/2024

"እኔ ለሀገሬ የሰላም ዘብ ነኝ"

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በክ/ከተማው ውስጥ ከሚገኙ ከሁሉም ወረዳዎች ከተውጣጡ የብልጽግና ፓርቲ ወጣት ሊግ አባላትና ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች ጋር "እኔ ለሀገሬ የሰላም ዘብ ነኝ" በሚል መሪ ቃል ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

 #እኔ ለሀገሬ የሰላም ዘብ ነኝ!
27/01/2024

#እኔ ለሀገሬ የሰላም ዘብ ነኝ!

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ታቦታት ወደ ማደሪያቸው ጉዞ ጀምረዋል።እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!ጥር 10/2016ዓ.ም
19/01/2024

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ታቦታት ወደ ማደሪያቸው ጉዞ ጀምረዋል።
እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!

ጥር 10/2016ዓ.ም

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Akaki kality woreda 8 prosperity party youths league - ብልጽግና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share