Ontex ኢትዮጵያ ሠራተኛች ትዝታ page

Ontex  ኢትዮጵያ    ሠራተኛች    ትዝታ   page Lesewhu

16/07/2025

የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፓርላማው ፍቃደኛ ከሆነ በስራ መውጫ ስዓት #ፌስታል ይዘው ከሆቴል ተመላሸ ምግብ የሚለምኑ ሰራተኞች መኖራቸውን ማሳየት እንደሚችል ተናገረ፡፡

ኮንፌዴሬሽን ይህን ያለው በቅርብ ይጸድቃል ተብሎ በሚጠበቀው የፌዴራል ገቢ ግብር ማሻሽያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

ከገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከሰራተኛው ለመቁረጥ የቀረበው ሃሳብ ውስብስብ የዋጋ ንረትን እና የድህነት መጠንን ያላገናዘብ ከመሆኑም በላይ ማጭበርበር ሳይኖር በአግባቡ ከደሞዙ ግብር የሚከፍለውን ሰራተኛ ከችግር የሚውጣ ሳይሆን ችግር ውስጥ የሚከት እንደሆነ የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ዋና ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ተናግረዋል፡፡

ሰራተኛው በቀን አንድ ጊዜ በልቶ መዋል አልቻለም ያሉት ፕሬዝዳንቱ ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ወጪዎች ስላሉበት ነው ብለዋል፡፡

ተቀጣሪው ሰራተኛ ህክምና ሄዶ መታከም የማይችልበት ሁኔታ ላይ ደርሷል ሲሉ ያስረዱት አቶ ካሳሁን እውነት ለመናገር አንድ ሰው በ5 ሺ ብር ደሞዝ ቤት ኪራይ ይከፍላል ፣ ይበላል፣ ልብስ ይለብሳል ፣ ህክምና ይሄዳል ብለዋል፡፡

ህክምናውን እንተው እየጸለየ ይኑር ፤ቤት ኪራይውንም እንተወው በበረንዳ በሰዎች ላይ በጥገኝነት ይኑር ግን በቀን አንድ ጊዜ እየበላ መኖር የለበትም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
አንድ ድርጅት ከትርፉ 35 በመቶ ግብር ይከፍላል ያሉት የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ዋና ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ሰራተኛውም 35 በመቶ ይከፍላል ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ነጋዴውም፣ ድርጅቱም ከትርፉ ነው እኮ 35 በመቶ የሚከፍለው ሲሉ ያስረዱት አቶ ካሳሁን ሰራተኛው ግን ከትርፉ ሳይሆን ከሚበላው ላይ ነው የሚከፍለው ይህ እንዴት ነው? እኩል ይሆናል ብለዋል፡፡

ስለሰዎች ስናስብ ልማት ለማስቀጠል ነው ያሉት አቶ ካሳሁን ልማት ያለ ሰው ሰው ያለ ልማት ሊኖሩ አይችሉም ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ስለዚህም የሰራተኛውንም ጫና የመንግስትን ዓላማ ታሳቢ ያደረገ የግብር ምጣኔ መጣል አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አሁን በማሻሻያው የግብር መነሻ 2000 ሺ ብር ሲሆን ምን ታሳቢ ተደርጎ ነው? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
አንድ ስልት ሲሰራ ሰውን ማኖር አለበት ያሉት አቶ ከሳሁን ይህ መነሻ ግን ታሳቢ አላደረገም ብለዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው እንደገና ከሚመለከታቸው ሰዎች ጋር ቢመካከር ሲሉ የጠየቁት አቶ ካሳሁን ፎሎ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኑሮን አልቻሉም፤ ቋሚ ኮሚቴው ፍቃደኛ ከሆነ ከስራ ሲውጡ ፌስታል ይዘው ሆቴል አካባቢ ቆመው ሲለምኑ አብረን ማየት እንችላለን ብሏል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር በኩሉ አዋጁ በይድረስ ይድረስ የተዘጋጀ ሳይሆን ሁለት ዓመት ጥናት ተሰርቶበት የተዘጋጀ ማሻሻያ ነው ብሏል፡፡

2000 ብር መነሻ የተደረገበት ምክንያት ደግሞ የመክፈል አቅማችን ዝቅተኛ ስለሆነ ነው ሲል አስረድቷል፡፡
መነሻን ከዚህ ከፍ ለማድረግ ቢፈለግ አገሪቱ ያላት ገቢ አይፈቅድም ወደፊት ገቢው እያደገ ሲሄድ ግን መነሻን ከፍ ማድረግ እንደሚችል የገንዘብ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ፍቃዱ ሆረታ የኑሮ ውድነቱ ግብር በመክፍል ብቻ የመጣ እንዳልሆነ ተናግረው በኢትዮጵያ ብቻም ያለ ችግር አይደለም ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ድኤታው ከውጭ የምናስገባቸውን መዳበሪያ ፣ ነዳጅ እና መሰል ግብዓቶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በሰዎች ላይ ጫና ይፍጥራል ብለዋል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት ደግሞ መንግስት ደሞዝ መጨመሩን የተናገሩት ሚኒስትር ዲኤታው መንግስት አቅም በፈቀደ መሰረት ድጋፍ አድርጓል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በገቢ ግብር ላይ ያለውም ጫናውን መቀነስ ነው እንጂ ማጥፋ እንዳልሆነ የተናገሩት አቶ ፍቃዱ ሆረታ በነባሩ አዋጅ ላይ መነሳትን ብናመለከት 600 ነው ወደ 2000 ያደገው በውይይት ተደርጎበት ነው ብለዋል፡፡

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የሞያ ማህበራት ተሳትፎ የተደረገ ማሻሻያ እንጂ ዝም ብሎ የመጣ ቁጥር እንዳልሆነም የገንዘብ ሚኒስቴር ተናግረዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር የግብር መነሻው ከተቀጣሪ ሰራተኛ አሁን ካቀረብነው ከፍ ካለ መንግስት ከፍተኛ ገቢ እንደሚያጣ ተናግሮ በተለይ በክልሎች ገቢ ላይ የበረታ ጫና እንደሚያሳድር ተናግሯል፡፡

ዘገባው የሸገር ሬዲዮ ነው።

16/07/2025
14/07/2025
04/10/2024

በምሥራቅ ሸዋ ሙዳ ቅዱስ ገብርኤል አጥቢያ 8 ኦርቶዶክሳውያን በግፍና በጭካኔ በታጠቁ ጽንፈኛ ኃይሎች ተገድለዋል፡

| በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት በሙዳ ቅዱስ ገብርኤል አጥቢያ 8 ( ስምንት ) ኦርቶዶክሳውያን በግና በጭካኔ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ በታጠቁ ጽንፈኛ ኃይሎች በግፍ መገደላቸው ተገልጿል፡፡

በሙዳ ሰንቀሌ ቀበሌ በሙዳ ቅዱስ ገብርኤል አጥቢያ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖችን የታጠቁ ኃይሎች ቅዳሜ በ18/2017 ዓ.ም ሌሊት ከየቤታቸው በመልቀም ይዘዋቸው የሄዱ ሲሆን ጀቢሳ በሚባል አነስተኛ ወንዝ ሥር በግፍ የሰማዕትነት ጽዋ እንዲቀበሉ አድርገዋቸዋል፡፡ በቦታው የደረሰው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት አስክሬናቸውን በክብር በማንሳት በቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አሳርፏቸዋል ፡፡

የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በክስተቱ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸው በሀገረ ስብከቱ እየተበራከተ የመጣውን የንጹሐን ግድያ በማስመልከት ከሚመለከታቸው የምሥራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪዎችና ከዞኑ የጸጥታ መዋቅር ጋር ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ለአካባቢው ምዕመናንና ለአደጋ ተጋላጭ ናቸው ተብለው በሚታሰቡ ቦታዎች ሁሉ ጥበቃና ከላላ እንዲደረግ በአጽንዖት ጠይቀዋል፡፡ የዞኑ አስተዳደርና የዞኑ የጸጥታ መዋቅር ይህ ዜና ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ለዞኑ የጸጥታ ኃይል ስምሪት በመስጠት በአካባቢው የሚገኙ የጸጥታ ኃይሎችን ለጊዜው በማሠር የማጣራት ሥራና በአካባቢው የኦፕሬሽን ሥራ እያካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ብፁዕነታቸው ከዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም አባቶች ግድያ ጀምሮ ያለ እረፍት ከሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል እንዲሁም የዞን አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡

በሀገረ ስብከቱ ከከተማ ወጣ ባሉ አካባቢዎች እየተፈጸመ የሚገኘው በደልና ግፍ ታሪክ ይቅር የማይለው በመሆኑ የሚመለከተው ሁሉ ለሰላም ጠንክሮ እንዲሠራና ይኽን መሠል ድርጊት ያለ ርኅራኄ የሚፈጽሙትን መቃወምና ድርጊቱን ማውገዝ የሚገባ ሲሆን የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከትም ሕይወታቸውን ላጡ ክርስቲያኖች ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት እንዲያሳርፍ በመመኘት ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው ኦርቶዶክሳውያን መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

Via ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ

19/05/2024

Address

ኢትዮጵያ
Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ontex ኢትዮጵያ ሠራተኛች ትዝታ page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share