15/06/2026
ቅጥረኝነት - የሕወሓት ሌላው መልክ
+++++++++++
| ቅጥረኝነት በዓለም አቀፍ ሕግና በፖለቲካ ሳይንስ ትርጓሜ፣ አንድ አካል ከተሟገተለት ብሔራዊ ዓላማ፣ ርዕዮተ-ዓለም፣ ለግል ወይም ለቡድን ቁሳዊ ጥቅም በጦርነትና በብጥብጥ ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚሳተፍበት ክስተት ነው።
ቅጥረኝነት የራሱ ባሕሪያት፣ መገለጫ ዓይነቶችና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች አሉት። የቅጥረኝነት ዋና ባሕሪ፣ ቅጥረኛ ኃይሎች ለሉዓላዊነትና ለሕዝብ ሰላም ደንታ የላቸው፤ ተልዕኳቸው የሚወሰነው በገንዘብ አቅራቢዎቻቸው ፍላጎት ላይ ነው። ርኅራኄ የሌለው የጭካኔ ርምጃ መውሰድ፤ የሕግ የበላይነትን አለማክበርና ግጭቶችን ማራዘም ዋና መገለጫዎቻቸው ናቸው።
በሌላ በኩል፣ በታሪክ ውስጥ ከነበሩት ግለሰብ ቅጥረኞች ጀምሮ በአሁኑ ወቅት ወደተደራጁ የግል የጦር ኩባንያዎች እና በሀገር ውስጥ ተወልደው ለውጭ ኃይሎች አጀንዳ ለሚሠሩ "የውስጥ ተላላኪዎች" ደረጃ አድጓል።
ይህ ዓለም አቀፍ ተሞክሮ በአፍሪካ (ለምሳሌ በሊቢያ፣ ኮንጎ እና ሴራሊዮን) እንዲሁም በመካከለኛው ምሥራቅ የታዩት የቅጥረኞች ተሳትፎዎች፣ ሀገራትን ወደ ማይወጡበት የቀውስ አዙሪትና ወደ መንግሥት አልባነት የገፈተሩ ነበሩ።
ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት ሊንኩን አሰተያየት መስጫ ሳጥን ውስጥ ይመልከቱ