ወሎየዋ ፐጅ

ወሎየዋ ፐጅ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ወሎየዋ ፐጅ, Women's clothes shop, Jeddah.

03/01/2023
02/01/2023

እውን ሙስሊሞች ካዕባን ያመልካሉን?
ያለዕውቀት ሙስሊሞችኮ ለካዕባ፣ ለሐውልት፣ ለጣኦት ወዘተ..... ነው የምትሰግዱት (ምታመልኩት) ለምትሉ እህት ወንድሞች የማያዳግም ምላሽ‼

“ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ ፤።”
— ዘፍጥረት 28፥22

እውን ሙስሊሞች ካዕባን ያመልካሉን?

☞ካዕባ የሰላት ቂብላ (አቅጣጫ) ነው እንጂ ካዕባን አናመልከውም፡

☞ #ቂብላ ማለት በስግደት ወቅት አለም ላይ ያሉ ሙስሊሞች በሙሉ ፊታቸውን ወደ አንድ ስፍራ (አቅጣጫ) የሚያዞሩበት አቅጣጫ (ቂብላ) ማለት ነው።

ማወቅ ያለብን ሁሉም ሙስሊሞች ስንሰግድ ወደ ካዕባ አቅጣጫ እንዞራለን እንጂ ካዕባውን በፍፁም አናመልከውም ፡፡

ምናመልከው ሆነ የምንሰግድለት ለሃያሉ ፈጣሪያችን ☞ለአላህ (ሱ.ወ) ብቻ ነው፡፡

አላህ ሱ.ወ በተከበረው ቃሉ በሱረቱል አል-በቀራህ ላይ እንዲህ ይለናል

«የፊትህን ወደ ሰማይ መገላበጥ በእርግጥ እናያለን፡፡ ወደምትወዳትም ቂብላ እናዞርሃለን፡፡ ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ (ወደ ካዕባ) አግጣጫ አዙር፡፡ የትም ስፍራ ብትኾኑም (ስትሰግዱ) ፊቶቻችሁን ወደርሱ አግጣጫ አዙሩ፡፡ እነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት መሆኑን ያውቃሉ። አላህም ከምትሠሩት ሥራ ዘንጊ አይደለም፡፡ (ሱረቱል አል-በቀራህ ምዕ.2 ቁ.144)

የስግደት አቅጣጫ ሙስሊሞች ወደ አንድ አቅጣጫ ዞረው የሚሰግዱ መሆናቸውን ክርስቲያኖች ሲተቹባቸው ና ሲያፌዙ በብዛት ይታያል።

ነገር ግን የዚህን ትእዛዝ (ወደ አንድ አቅጣጫ ዞሮ የመስገድን) ምንጭ እስኪ ከመጽሃፍ ቅዱስ እናጢነው።

በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ በብሉይ ኪዳን አንድ የሰለሞን ጸሎት አለ
እንዲህም ይነበባል

☞{1ኛ ምጽሃፈ ነገስት 8፥44 ፧ጠላቶችህን ለመውጋት እንዲዘምቱ ህዝብህን የምታዝበት ጊዜ ጊዜ በሰማይም ሆነህ ጸሎታቸውን እና ልመናቸውን
በመስማት ።፧}

እዚህ ጋር እንግዲህ በግልጽ እንደምንመለከተው ወደ ተመረጠችው ቤተ መቅደስ እስራኤላውያን ፊታቸውን አዙረው ከጸለዩ ጸሎታቸው በከንቱ እንዳይቀር ና ድልም እንደሚቀናጁ ነብዩ ሰለሞን (ዓ.ሰ) መጸለያቸውን ነው✔።

ይህ ፊትን ወደ አንድ አቅጣጫ አዙሮ መስገድ በአዲስ ኪዳን በኢየሱስ ክርስቶስም ጊዜ የነበረ ሲሆን በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ ተዘግቦ ይገኛል።

☞ {ዩሃንስ ወንጌል 4፥19 ፦ ሴቲቱም ጌታ ሆይ አንተ ነብይ እንደሆንክ አያለሁ። አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ እናንተም ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ አለችው እየሱስም እንዲህ አላት
☞ ወይም አላት።

በዚህ ጥቅስ ውስጥ ደግሞ እንደምንመለከተው እየሱስ ክርስቶስ (ዓ.ሰ) ይህ የጸሎት አቅጣጫ እንደሚቀየር መተንበያቸውን ነው።

{አንቺ ሴት እመኚኝ በዚህ ተራራ ወይም በእየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል። }

ይህ ትንቢት ኢየሱስ ክርስቶስ (ዓ.ሰ) የነብያችንን (ሰዐወ) መምጣት ከተነበዩበት ትንቢት መካከል አንዱ ነው።
ምክንያቱም ይህ ትንቢት ፍጻሜውን ያገኘው በነብያችን ሙሀመድ (ሰዐወ) አማካኝነት ነው።

እንደሚታወቀው በመዲና ውስጥ መስጂደል ቂብለተይን የሚባል መስጅድ አለ ትርጉሙም ባለ ሁለት ቂብላው (የስግደት አቅጣጫ) መስጂድ ማለት ነው።

መስጂዱ እንዲህ ተብሎ የተሰየመበት ምክንያትም። ነብዩ ሙሀመድ (ሰዐወ) መጀመርያ በዚያ መስጅድ ውስጥ ፊታቸውን ወደ በይቱል መቅዲስ (ቤተ-መቅደስ) ማለትም ወደ እየሩስአሌ

Address

Jeddah

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወሎየዋ ፐጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share