21/01/2026
ግብፅ የበላይነቷን በኢትዮጵያ መቀማቷ ተረጋግጧል!
ግብፅ ናይል ወንዝ የራሷ እንደሆነ በፕሮፓጋንዳ ከዜጎቿ እስከ ሃያላኗ ድረስ አሳምነው ለዘመናት የኖረችውን በኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምክንያት የበላይነቷን ተቀምታለች።
ማታ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ላይ
✍️"ኢትዮጵያ ከዓለም እንኳን ትልቅ የሚባል ግድብ አላት"
✍️"እኔ ናይል ሲባል የማውቀው ግብጽን ነው እንጂ ኢትዮጵያን አልነበረም ፣
✍️"ግብጾች በቂ የውሀ መጠን የላቸውም!"
✍️ ግብፆች ናይልን ለመዝናኛ፣ ለጉዞ እና ለቱሪዝም ይጠቀሙበታል" በማለት የግብፅን ስጋት አጉልተው ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ ትራሞፕ ግብፅን እንደ ማገዝ አድርገው ያወራው ቢሆንም ኢትዮጵያ ከግብፅ የበላይነቷን እንደቀመችው የሚያሳይ ንግግር ሆኖ ተይተዋል።
ግብፅ ለዘመናት በአፍሪካ ብሎም እጅ በመላክ በምስራቅ አፍሪካ አካባቢ የነበራት ተሰምነቷ እየከሰመ መምጣቱ እየተረጋገጠ መጥተዋል።
በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የሄደችበት ሁሉ ውጤት አልባ ሆነውም ለዓለም ግልጽ ሆነው ተይተዋል።
አሁን ወደ አሜሪካ አደራድሩኝ እያለች የሄደችው ከእዚህ በኋላ ብዙም ለውጥ ማምጣት እንዳማትችል ታውቃለች። ግን ኢትዮጵያ እንደ ወሳኝ አጀንዳ አድርጋ ለያዘችው የባህር በር ጥያቄ እንዲጓተት ልታደርግ ትችል ይሆናል።
@ፍፁም ተስፋዬ(Erbeeto)